ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የሕግ ባለሙያዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠበቆች ላይ ተጥሎ የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ አገደ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የሕግ ባለሙያዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠበቆች ላይ ተጥሎ የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ አገደ።
የሕግ ባለሙያዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠበቆች ላይ ተጥሎ የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ አገደ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገቢዎች ቢሮ፣ የሕግ ባለሙያዎች (ጠበቆች) ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ጋር በተያያዘ ላቀረቡት አቤቱታ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አሳውቋል።

ቢሮው ለዞንና ለከተማ አስተዳደር የገቢ መሥሪያ ቤቶች ባስተላለፈው ማብራሪያ ፣ በጥብቅና ስራ የተሰማሩ የሕግ ባለሙያዎች በገንዘብ ሚኒስቴር በወጣው መመሪያ ቁጥር 1104/2018 መሠረት ለተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲመዘገቡ ተሰጥቶ የነበረው ድንጋጌ ላይ የመመሪያ ክለሳ አቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ነበር።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ፣ ጠበቆች ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲመዘገቡ የሚያዘውን መመሪያ በጠበቆች ላይ ተፈጻሚ እንዳይሆንና በዕግድ እንዲቆይ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በመሆኑም በፍርድ ቤቱ የተለያዩ መዝገቦች የታገዱ ጉዳዮች መኖራቸውን ቢሮው አረጋግጧል።

ነገር ግን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባው በዕግድ መቆየቱ፣ ጠበቆችን ከሌሎች የግብር ግዴታዎች ነፃ እንደማያደርጋቸው ያሳሰበው ቢሮው ማንኛውም የሕግ ባለሙያ (ጠበቃ) የንግድ ሥራ ገቢ ግብሩን በተመለከተ በክልሉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 301/2018 መሠረት የመክፈል ግዴታው እንደጸና ነው ብሏል።

ባለሙያዎቹ እንደ ደረጃ "ለ" ግብር ከፋይነታቸው የሒሳብ መዝገብ የመያዝ ወይም በታወቀው የገቢ ማሳወቂያ ቅጽ (Form) መሠረት ግብራቸውን በወቅቱ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ነው ያለው።

ይህ የፍርድ ቤት ዕግድ የሚያገለግለው ከተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ጋር ለተያያዘው ጉዳይ ብቻ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፣ የንግድ ሥራ ገቢ ግብራቸውን በሒሳብ መዝገብ የማያሳውቁ ጠበቆች እንደግብር ከፋይነታቸው ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም ወይም ከህዳር 1/2019 ዓም ጀምሮ በሦስተኛ ወገን ወይም በግምት የንግድ ስራ ገቢ ተወስኖ እንዲያሳውቁ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚገባቸው ግብር ከፋዮችም ግዴታቸውን ካልተወጡ በአዋጁ የተደነገጉ አስተዳደራዊ ቅጣቶችም ተፈጻሚ እንደሚሆኑባቸው አሳውቋል።

በሌላ በኩል የፌደራል ጠበቆች ማህበር የጠበቆችን የግብር አከፋፈል ሁኔታ በተመለከተ እያከናወናቸው ስላላቸው ስራዎች ለአባላቱ በሰጠው ማብራሪያ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን እያደረገ ስለመሆኑ አንስቷል።

ማህበሩ ጠበቆች ከ«ለ» ደረጃ ግብር ከፋይነት ውጪ ተደርገው የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚጠየቁበትን አዲሱን አሰራር በመርህ ደረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ያምናል ያለ ሲሆን ይህም በሕግ ማሻሻያ ሊታረም የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ከመንግስት አካላት ጋር በቀጣይነት እያነሳ ይገኛል ብሏል።

በዚህ ምክንያት መመሪያው እስኪወጣ ድረስ ጠበቆች እንደ ቀድሞው አሰራር በተመጣጣኝ የገቢ መቶኛ ተቀናሽ ስሌት መሠረት ግብራቸውን እንዲከፍሉ ጊዜያዊ አሰራር እንዲፈቀድ ማህበሩ መጠቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማህበሩ ከሰጠው ማብራሪያ ላይ ተመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች