የመቐለ ዓቃቤ ሕግ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ ጠየቀ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የመቐለ ዓቃቤ ሕግ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ ጠየቀ።
ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተያይዞ የተሰጠውን የሁለቱን ተከሳሾች " ነጻ ናችሁ " የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማቅረቡን የመቐለ ከተማ ዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ታደሰ ባይሩ የመቐለ ማዕከላይ ፍርድ ቤት በዘውዲ ሃፍቱ ግድያ ተከሰው በነበሩ ግለሰቦች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ ሰጥቶ መዝገቡን ዘግቶ እንደነበር ገልጸዋል።
ነገር ግን ተከሳሾቹ ለሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረቡት ይግባኝ በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ኃላፊው ጠቁመዋል። ዓቃቤ ሕግም ውሳኔውን እንደማይቀበል በመግለጽ ለትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረቡን አስረድተዋል።
ታደሰ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹን በነፃ የሚያሰናብተው ውሳኔ አግባብ አይደለም በሚል እና የቀደመው ውሳኔ በዳኞች 2 ለ1 ድምፅ መሻሩን በመጥቀስ ይግባኙ ቀርቧል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ “ማስረጃ ጠፍቷል” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ግን ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑን የዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ገልጸዋል።
በተጨማሪም፣ ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ሁለቱ ግለሰቦች በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ መኖራቸውንም ሆነ አለመኖራቸውን እንደማያውቁ አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia