የሰውን እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ምራቅ እየተፉ " ልጠርግልህ " በማለት በተለምዶ " ትፍታ " የሚባለውን የስርቆት ወንጀል የሚፈፅሙ አንዳንድ ግለሰቦች ስላሉ በንብረታችሁ ላይ ጥንቃቄ እን…
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የሰውን እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ምራቅ እየተፉ " ልጠርግልህ " በማለት በተለምዶ " ትፍታ " የሚባለውን የስርቆት ወንጀል የሚፈፅሙ አንዳንድ ግለሰቦች ስላሉ በንብረታችሁ ላይ ጥንቃቄ እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
ነገሩ እንዲህ ነው ....
ተጠርጣሪዎቹ ፦
- አብዱልራዛቅ አገዢ፣
- ግዜያለሁ ተሻገር፣
- ይተያሁ ምንተስኖት እና አብዲ መሐመድ ይባላሉ።
የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ/ም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረደ 7 ልዩ ቦታው " ግዮን መድኃኒት ቤት " አካባቢ ከቀኑ 6:00 ሠዓት ገደማ ነው ።
በዕለቱ አንድ የቻይና ዜጋ ከቸርችል ወደ መስቀል አደባባይ በእግራቸው እየተንቀሳቀሱ ነበር።
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አብዱልራዛቅ አገዢ የተባለው ወደ ግለሰቡ ቀርቦ ምራቅ ይተፋበታል።
በመቀጠልም " ቆይ ልጠርግልህ " በማለት ከለበሰው ጃኬት ውስጥ የዋጋ ግምቱ 360 ሺህ የሚያወጣ Iphone Pro Max 17 ሞባይል ይዞ ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር የሠሌዳ ቁጥሩ ባልታወቀ ቪትስ ተሽከርካሪ ከአካባቢው ይሰወራሉ።
የግል ተበዳይ የተፈጸመባቸውን ወንጀል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የለገሃር አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ያመለክታሉ።
ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ክትትል አንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ውስጥ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3B83359 አ/አ በሆነ ቪትስ ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
ሞባይሉን ለማስመለስ በተከናወነ የምርመራ ተግባር አብዱልራዘቅ አገዢ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ላይ በተደረገ ፍተሻ ንብረቱን በምሪት ማስመለስ ችሏል።
ሰው ላይ ምራቅ በተመትፋትና " ልጥረግልህ/ልጥረግልሽ " በማለት የስርቆት ወንጀል የሚፈጽሙ ስላሉ ተጠንቀቁ።
መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia