የአሜሪካ ዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS) በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ቢሮውን ነገ ይከፍታል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የአሜሪካ ዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS) በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ቢሮውን ነገ ይከፍታል።
ቢሮው ከነገ ጀምሮ ሥራ የሚጀምር ሲሆን በኢትዮጵያ ከUSCIS ጋር የተያያዙ የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን ይመለከታል።
በቢሮው በኩል የውጭ ሀገር ሰነዶች ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣ የማጭበርበር ጥርጣሬዎችን መመርመር እና የቤተሰብ ዝምድናን ለማረጋገጥ የDNA ምርመራ ናሙና መሰብሰብ ይከናወናል።
USCIS እንዳለው፣ እስካሁን እነዚህ ሥራዎች በአብዛኛው ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጋር በመተባበር ይከናወኑ ነበር። አዲሱ ቢሮ ግን USCIS እነዚህን ሂደቶች በቀጥታ በኢትዮጵያ እንዲያከናውን ያስችለዋል።
ነገር ግን ይህ ማለት በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚነዛው " የአሜሪካ ቪዛ ማግኘት ቀላል ሆኗል " ማለት አይደለም።
አዲሱ የUSCIS ቢሮ በዋናነት የሰነድ ማረጋገጫ፣ የማጭበርበር ምርመራ እና የቤተሰብ ዝምድና ማረጋገጫን ጨምሮ የኢሚግሬሽን ሂደቶችን ለመደገፍ ነው።
ቢሮው የቪዛ መስጫ ቢሮ አይደለም፤ የቪዛ ማመልከቻና ውሳኔ ሂደትም ከዚህ በተለየ የአሜሪካ የቆንስላ ሥርዓት ውስጥ ይቀጥላል።
እንዲሁም የUSCIS አዲሱ ቢሮ አገልግሎቶችን በቀጠሮ ብቻ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia