ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአዲስ ዓመት በዓልን የተመለከተ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአዲስ ዓመት በዓልን የተመለከተ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአዲስ ዓመት በዓልን የተመለከተ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

የ2019 አዲስ አመት በዓልን አስመልክቶ ከእሳትና ኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ መጨመር፣ ሰፊ መዝናናት አንፃር ሊከሰቱ የሚችሉ የእሳት ቃጠሎ እና ሌሎች አደጋዎችን ቅድሚያ ለመከላከል እንዲቻል በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ለማህበረሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቱን ገልጿል።

ከኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ አቶ ሰሎሞን መኮንን በሰጡን ገለጻ፣ በበዓል ወቅት፣ በመኖሪያ ቤት እና ምግብ በሚያሰናዱ ተቋማት የጧፍ፣ የጋዝ እና የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን አግባብ ባልሆነ መንገድ ከመጠቀም መጠንቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የከሰል ምድጃ በቤት ውስጥ ጥቅም ላይ በሚውልበት ወቅት፥ በርና መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር ማድረግና ምድጃው አገልገሎቱን ሲጨርስ ወደ ውጭ አውጥቶ ቤቱን በሚገባ ማናፈስ እንዳይረሳም አስጠንቅቀዋል።

አቶ ሰለሞን አክለው ፦

- ለበዓሉ ማድመቂያ የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና መብራቶችን በሙቀት ኃይል ቀልጠው እሳት እንዳያስከትሉ እየተቆጣጠሩ መጠቀም፣

- ሻማ እና ጧፍን ለመብራት አገልግሎት መጠቀም ቢያስፈልግ ተቀጣጣይ መሳሪያዎችን ከአጠገባቸው ማራቅ፣

- በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰሩ የተለያዩ መሳሪያዎች መስኪያዎችን በአንድ ሶኬት ላይ ደራርቦ አለመጠቀም፣

- የኤሌክትሪክ እሳት ቢነሳ ኃይሉ ከምንጩ ሳይቋራጥ በውሃ ለማጥፋት አለመሞከር፣

- እሳት ስራ ላይ ከሚውልበት አካባቢ በቀላሉ ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ተቀጣጣይ ነገሮችን ማራቅ ሽቶና የመጥፎ ጠረን ማጥፊያ ፍሊቶችን ከመርጨት መቆጠብ፣

- ከበዓሉ መዝናናት ጋር ተያይዞ በየአካባቢው የሚዘጋጀው ካምፕ ፈየርም በተለይ ለእሳት አስጊ በሆኑ በነዳጅ ዴፖዎች፣ በነዳጅ ማዳዎች፣ በመኖሪያ መንደሮች እሳት አደጋ እንዳያስከትል፣

- በዓሉን አስመልክቶ በሚደረግ መዝናናት፣ እንዲሁም፥ ጠጥቶ መኪና ከማሽከርከር መቆጠብ.... ሊደርስ ከሚችለው የህይወትና ንብረት አደጋ ራስን መጠበቅ መሆኑን ተገንዝቦ የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሰሞንኛው የመርካቶ የእሳት አደጋ መንስኤና የጉዳት መጠን ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን፣ አቶ ሰለሞን፣ ዝርዝር መረጃውን አደጋውን ከተቆጣጠረው የአደጋ ምላሽ ዘርፍ ጋር ተነጋግረው እንደሚያሳውቁ ጠቁመዋል።

N.B/ ማንኛውም የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ፣ በአደጋ ለተጎዱ እንዲሁም ከሌሎች ድንገተኛ ህመሞች በተጨማሪ ለወላድ የድንገተኛ ህክምናና አምቡላንስአገልግሎትበነፃ መስመር 939በቀጥታ መስመሮች 011-1-55 53 00/ 011-1-56 86 01 ለኮሚሽኑ እንድትደውሉ መልዕክት ተላልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች