የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ እና በቅዳሜ ቀናት ለሚሰሩ ሠራተኞች የትራንስፖርት አበል አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ እና በቅዳሜ ቀናት ለሚሰሩ ሠራተኞች የትራንስፖርት አበል አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል።
በመመሪያው መሠረት በቅዳሜ ቀን ለሚሰሩ ሠራተኞች በቀን 200 ብር (በወር 800 ብር) እንዲሁም በምሽት ለሚሰሩ የትራንስፖርት መመለሻ በቀን 100 ብር (በወር 2,200 ብር) ተመድቧል። በዚህም መሠረት አንድ ሠራተኛ በወር እስከ 3,000 ብር የትራንስፖርት አበል ማግኘት ይችላል።
የትራንስፖርት አበል የሚከፈለው ከመደበኛ ሰዓት በኋላ አገልግሎት ለሚሰጡ ሠራተኞች፤ በቅዳሜ ቀናት በተፈቀደ የሥራ መርሐ-ግብር መሠረት ለሚሰሩ ሠራተኞች ብቻ ነው።
- በረዥም ጊዜ ሥልጠና ወይም ትምህርት ላይ ለሚገኝ ሠራተኛ፤
- በተፈቀደው የሥራ መርሐ-ግብር መሠረት በሥራ ላይ ላልተገኘ ሠራተኛ፤
- ተቋሙ የጋራ ወይም በተናጥል ትራንስፖርት አገልግሎት ላቀረበለት ሠራተኛ እና በተመሳሳይ ዓላማ ከሌላ ምንጭ የመጓጓዣ ድጋፍ የሚያገኝ ሠራተኛ የዚህ ትራንስፖርት አበል ተጠቃሚ አይሆንም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀምሌ 21 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia