የዝናብ እጥረት
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የዝናብ እጥረት
በትግራይ ክልል በማዕከላዊና ምስራቃዊ ዞኖች የሚገኙት የአበርገለ እና የኢሮብ ወረዳዎች እስካሁን የክረምት ዝናብ ባለማግኘታቸው፣ በ21 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት የሚኖሩ ነዋሪዎችና እንስሳት ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።
በአበርገለ ወረዳ የሚገኙ 13 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት እስካሁን የክረምት ዝናብ ያላገኙ ሲሆን፣ በኢሮብ ወረዳ የሚገኙ 8 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ደግሞ የክረምት ዝናብ ፈጽሞ አልጀመረም ተብሏል።
በዝናብ እጥረቱ ምክንያት እንስሳት ለግጦሽና መኖ እጥረት ሲጋለጡ፣ ነዋሪዎችም ለመጠጥ ውሃ ከፍተኛ እጥረት እያጋጠማቸው መሆኑ ተገልጿል።
በ21 ቀበሌዎቹ የሚኖሩ ነዋሪዎች ራሳቸውንና እንስሳቶቻቸውን ከከፋ አደጋ ለመታደግ የመንግሥትና የሰብዓዊ ድርጅቶች አስቸኳይ ድጋፍ ጠይቀዋል።
በተለይም በኢሮብ ወረዳ የሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች ላለፉት ስድስት ዓመታት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር መቆየታቸው፣ አሁን ከተከሰተው የዝናብ እጥረት ጋር ተዳምሮ የህዝቡን ስጋት እንዳባባሰው የመረጃ ምንጮች ያስረዳሉ።
እንደ ታማኝ የመረጃ ምንጮች በኢሮብ ወረዳ ፦
- የዓገረለኹማ፣
- ኣራዕ፣
- ዓሊቴና፣
- ወርዓትለ፣
- እንዳሞሳ፣
- ሓረዘ ሰብዓታ፣
- እንዳልጌዳ እና ደውሃን ቀበሌዎች እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የክረምት ዝናብ አለማግኘታቸው ተመላክቷል።
በአካባቢዎቹ ያለው የደረቅ ሁኔታ በሰውና በእንስሳት ላይ ያደረሰውን ሙሉ ተፅዕኖ በባለሙያዎች ለመገምገም እስካሁን እንዳልተቻለ ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia