የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል።
በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር ተወስኗል።
በተጨማሪም፦
- የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 500 ብር የምዝገባና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።
- የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ፦ ለኢትዮጵያውያን 950 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።
- የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 1,000 ብር የምዝገባና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 150 ዶላር።
- የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ፦ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 115 ዶላር።
- ምትክ ሰርተፊኬትና ማረጋገጫ፦ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 170 ዶላር።
- የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ/ማጣራት፦ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 75 ዶላር።
- በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል ፦ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 130 ዶላር።
- ኦፊሴላዊ ትራንስክሪፕት መላክ ፦ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 50 ዶላር።
የፈተና ውጤት መረጃን ለምርምር ለሚጠይቁ ተቋማት በአንድ ጥናት 10,000 ብር፣ ለውጭ ተቋማት 1,875 ዶላር ክፍያ ተወስኗል። ለግለሰቦች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን 1,000 ብር፣ ለውጭ ዜጎች 190 ዶላር እንደሚከፈል ተገልጿል።
በተጨማሪም ያገለገሉ የምዘና መሳሪያዎችን ለመጠቀም ከጠቅላላ ወጪው 5 በመቶ፣ አዲስ የምዘና መሳሪያ ለማዘጋጀት ደግሞ 10 በመቶ ክፍያ እንደሚፈጸም ደንቡ ያስቀምጣል።
ደንቡ ለሌሎች የምዘናና የማረጋገጫ አገልግሎቶችም አዳዲስ የክፍያ ተመኖችን አካቷል።
የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia