ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የገቢዎች ሚኒስቴር የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ለእያንዳንዱ የንግድ ስራ መስክ በተናጠል እና ሁሉንም የንግድ መስኮች ያካተተ የተጠቃለለ ሪፖ…

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የገቢዎች ሚኒስቴር የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ለእያንዳንዱ የንግድ ስራ መስክ በተናጠል እና ሁሉንም የንግድ መስኮች ያካተተ የተጠቃለለ ሪፖ…
የገቢዎች ሚኒስቴር የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ለእያንዳንዱ የንግድ ስራ መስክ በተናጠል እና ሁሉንም የንግድ መስኮች ያካተተ የተጠቃለለ ሪፖርት ማቅረብ እንዳለባቸው አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳሰበ።

የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከአንድ በላይ የንግድ መስክ ላይ ለተሰማሩ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ለእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ የተለየ የሂሳብ መዝገብ መያዝ እንዳለባቸው አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

ይህ አሰራር ተግባራዊ የሚደረገው በገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 86 እና በሠንጠረዥ "ሐ" በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት ነው።

በአዋጁ ድንግጌ ከአንድ በላይ በሆኑ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች፣ የሙያ አገልግሎት የሚሰጡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡና በፈቃደኝነት መዝገብ የሚይዙ የደረጃ "ለ" ግለሰብ ግብር ከፋዮች ለእያንዳንዱ የንግድ መስክ የተለየ የሂሳብ መዝገብ፣ ደጋፊ ሰነዶች እና የግብር ማስታወቂያ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል።

ይህንን የህግ ድንጋጌ በስራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ የግብር ማስታወቂያ ቅጾች የመንግስት ታክስ አስተዳደር ስርዓት (SIGTAS) ላይ በማልማት ሂደት ላይ እንደሚገኝ የገቢዎች ሚኒስቴር በየደረጃው ለሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ከላከው ሰርኩላር ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።

የሚኒስቴሩ የግብር አስተዳደር ሥርዓት (SIGTAS) አዲሱን አሰራር ለማስተናገድ በልማት ላይ በመሆኑና በማሻሻያ አዋጁ መሰረት ስራው ተጠናቆ ሲስተሙ እስኪለቀቅ ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሂሳብ መዝገብ የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች እስከ ጥቅምት 30/2019 ዓም ድረስ ጊዜ ቢኖራቸውም በተለያየ ምክንያት ግብራቸውን ለማሳወቅ የሚመጡ ግብር ከፋዮች በማንዋል የተዘጋጁ ቅጾችን እንዲጠቀሙ ጠይቋል።

ግብር ከፋዮች የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ለእያንዳንዱ የንግድ ስራ መስክ በተናጠል እና ሁሉንም የንግድ መስኮች ያካተተ የተጠቃለለ ሪፖርት ማቅረብ እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

በሲስተሙ ላይ የሚደረገው የማበልጸግ ሥራ እንደተጠናቀቀ፣ ግብር ከፋዮች ያስገቡት መረጃ ወደ ኮምፒውተር ሥርዓቱ እንደሚገባና ከዚያ በኋላ በእጅ የሚሞላ ማስታወቂያ ተቀባይነት እንደማይኖረው ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች