ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የጾመ ፍልሰታ ለማርያምን በማስመልከት የምህላ ሥነ-ሥርዓት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት በተከታታይ እንደሚካሄድ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ቅድስት አክሱም ጽዮን አስተዳደር አስታወቀ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የጾመ ፍልሰታ ለማርያምን በማስመልከት የምህላ ሥነ-ሥርዓት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት በተከታታይ እንደሚካሄድ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ቅድስት አክሱም ጽዮን አስተዳደር አስታወቀ።
የጾመ ፍልሰታ ለማርያምን በማስመልከት የምህላ ሥነ-ሥርዓት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት በተከታታይ እንደሚካሄድ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ቅድስት አክሱም ጽዮን አስተዳደር አስታወቀ።

የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ባስተላለፈው መልእክት፥ ምእመናንና ምእመናት በምህላና በጸሎት በአንድነት ፈጣሪያቸውን እንዲለምኑ ጥሪ አቅርቧል።

በቅርብና በሩቅ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ምእመናንና ምእመናት በጸሎት እንዲተጉና እንዲተባበሩም አደራ ብሏል።

" ልዑል እግዚአብሔር ጸሎትና ምህላችን ይድረሰው፤ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ሰላምና ምሕረቱን ይላክ " በማለት መንፈሳዊ ምኞቱን አስተላልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች