ድሮን ማብረር ተከለከለ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ድሮን ማብረር ተከለከለ
በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ የድሮንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ማሳሰቢያ ፤ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በአዲስ አበባ እና አከባቢው ማንኛውንም አይነት ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ ገልጿል።
አገልግሎት መ/ቤቱ፤ " እንደ ወትሮው ሁሉ በአዲስ አበባና አካባቢው የሚንቀሳቀሱ ድሮኖችንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላትን የሚቆጣጠር የተቀናጀ የጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል " ብሏል።
የተሰጠውን ማሰሰቢያ በመጣስ የሚነሱ እንዲሁም በየትኛውም አካባቢና ከፍታ የሚበሩ ድሮኖችን በመለየት፣ በመጥለፍ እና ወደ አስፈላጊው ቦታ በማሳረፍ እንዲሁም የአብራሪዎቹን ትክክለኛ መገኛ ቦታ በመለየትና በቁጥጥር ስር በማዋል ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
ከዚህ ቀደም በሥራ ምክንያት ድሮኖች መጠቀም የሚፈልጉ አካላት ፦
- የበረራውን ዓላማ፣
- የሚበርበትን ቦታ፣
- የድሮኑን አይነት እና የሞዴል ቁጥር በመጥቀስ አስቀድመው ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በመጠየቅ እና ፈቃድ በማግኘት ሲጠቀሙ እንደነበር ያስታወስው መ/ቤቱ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን እና ብሔራዊ ኩነቶችን ደኅንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ለመወጣት ላልተወሰነ ጊዜ ፍቃድ መስጠቱንና የበረራ ክልከላውን ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ የመጡ ድሮኖች እና መሰል ቴክኖሎጂ ወለድ መሣሪያዎች የሚፈጥሯቸውን የብሔራዊ ደኅንነት ስጋቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ታጥቂያለሁ ፤ ብቁ የሰው ኃይልም አፍርቻለሁ " ያለው መ/ቤቱ " የተላለፈውን ማሳሰቢያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚያስፈጽም ገልጿል።
መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvaethiopia