ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ግድባችንን ለመገንባት አንፈራም " - ደቡብ ሱዳን

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ግድባችንን ለመገንባት አንፈራም " - ደቡብ ሱዳን
" ግድባችንን ለመገንባት አንፈራም " - ደቡብ ሱዳን

ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ " የፉላ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት "ን ለማስጀመር ዝግጅት ላይ ነኝ አለች።

የሀገሪቱ መንግሥት የግድቡን ግንባታ ለማካሄድ ከግብፅ በኩል የሚመጣ ምንም ዓይነት ፍራቻ እንደሌላት አሳውቋል።

ደቡብ ሱዳን በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመች ያለችው ከአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟ አንድ በመቶ ያህሉን ብቻ ነው። ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት አቆይቷል።

ኒሙሌ በሚባል አካባቢ ይገነባል የተባለው የፉላ ግድብ 1,800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የደቡብ ሱዳንን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ማሟላት ያስችላል። ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ትርፍ ኃይል ያመነጫል።

ሀገሪቱ ይህን ግድብ ለመንገንባት በግብፅ በኩል የሚመጣ ምንም አይነት ፍራቻ እንደሌለባት  አሳውቃለች።

" ግድባችንን ለመገንባት ምንም አንፈራም " ስትል ነው በይፋ የገለጸችው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine

ተዛማጅ ታሪኮች