ለብራዚል ተጨማሪ አቅም የሰጣት ኩንያ !

ለብራዚል ተጨማሪ አቅም የሰጣት ኩንያ !
አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በመክፈቻው ጨዋታ ኢጎር ቲያጎን የመጀመሪያ ምርጫቸው አድርገው ነበር።
ይሁን እንጂ የብራንትፎርዱ አጥቂ ኢጎር ቲያጎ በጨዋታው ለስልሳ ደቂቃዎች ሜዳ ላይ ቢቆይም ተቸግሮ ታይቷል።
ማቲውስ ኩንያ በቋሚነት በተሰለፈባቸው ቀጣይ ጨዋታዎች ቡድኑ ድል ሲያደርግ ከቪንሰስ ጁኒየር ጋርም ጥሩ ጥምረት ፈጥሯል።
ኩንያ ሀይቲ ላይ ሁለተኛውን ማራኪ ጎል ሲያስቆጥር ቪንሰስ ጁኒየር ነበር አመቻችቶ ያቀበለው።
ግቡ የሁለቱን ተጨዋቾች ጥሩ ጥምረት እንዲሁም የማቲውስ ኩንያን የአጨራረስ ብቃት ያሳየ ነበር።
የማንችስተር ዩናይትዱ ተጨዋች ማቲውስ ኩንያ በስኮትላንድ ጨዋታ ተጨማሪ ግብ አስቆጥሮ በአለም ዋንጫው ያለውን ግብ ሶስት አድርሷል።
@tikvahethsport @YisakAH