ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሊዮኔል ሜሲ የጥቃት ኢላማ እንደነበር ተገለፀ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሊዮኔል ሜሲ የጥቃት ኢላማ እንደነበር ተገለፀ !
ሊዮኔል ሜሲ የጥቃት ኢላማ እንደነበር ተገለፀ !

የአሜሪካ ፖሊስ በ 2026 አለም ዋንጫ ወቅት በርካታ የጥቃት ስጋቶችን እንዳከሸፈ አስታውቋል።

አብዛኞቹ የጥቃት ስጋቶች አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ላይ ያነጣጠሩ እንደነበሩ ነው ፖሊስ ያሳወቀው።

አርጀንቲና ከግብጽ እና ጆርዳን ጋር ካደረገችው ጨዋታ በፊት ስታዲየም ውስጥ ቦምብ እናፈነዳለን የሚል ዛቻ ለፖሊስ ደርሶት ነበር ተብሏል።

ተጠርጣሪው " በላዬ ላይ ቦንብ ታጥቄ ወደ ሜዳ በመግባት ሜሲን አጠቃለሁ " የሚል መልዕክት መላኩ ተነግሯል።

በተጨማሪም በተለያዩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች ውስጥ ቦምብ አስቀምጠናል የሚል መልዕክት መድረሱ ተገልጿል።

ፖሊስ አነፍናፊ ውሾችን በማሰማራት አሰሳ ቢያደርግም በስታዲየሙ ምንም ነገር እንዳላገኘ እና ሀሰተኛ ማስፈራሪያ እንደነበር ገልጿል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች