ሞሀመድ ሳላህ ለምሽቱ ጨዋታ ይደርሳል !

ሞሀመድ ሳላህ ለምሽቱ ጨዋታ ይደርሳል !
ግብፃዊው ኮከብ ሞሀመድ ሳላህ ባለፈው የኢራን ጨዋታ የ ሀምስትሪንግ ጉዳት ገጥሞት ተቀይሮ ወጥቶ ነበር።
ይሁን እንጂ ሳላህ ለዛሬው የአውስትራሊያ ጨዋታ ብቁ መሆኑን የፈርዖኖቹ አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን አሳውቀዋል።
ሞሀመድ ሳላህ በጨዋታው ምናልባት ቋሚ ሆኖ ላይጀምር እንደሚችል አሰልጣኙ ጠቁመዋል።
ሳላህ በዚህ ሳምንት የህክምና ምርመራ ካደረገ በኋላ በቡድኑ ልምምድ ላይ በከፊል እንደተሳተፈ ተነግሯል።
ሳላህ በምድብ ጨዋታዎች አንድ ጎል አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ በማቀበል ሀገሩ ጥሎ ማለፉን እንድትቀላቀል ረድቷል።
ሆሳም ሀሰን ሳላህ በውድድሩ ያሳየውን አቋም በማድነቅ “ ከእሱ ጋር በመስራቴ እድለኛ ነኝ ” ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe