ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ በአለም ዋንጫው ታሪክ ፅፊያለሁ ” ኪሊያን ምባፔ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ በአለም ዋንጫው ታሪክ ፅፊያለሁ ” ኪሊያን ምባፔ
“ በአለም ዋንጫው ታሪክ ፅፊያለሁ ” ኪሊያን ምባፔ

“ ሰዎች በየመንገዱ ባሎን ዶር ማሸነፍ አለብህ እያሉኝ ነው ”

የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ስለሚነሳበት የመከላከል ክፍተት ተጠይቆ ነበር።

ጋዜጠኞች ለምባፔ ራፊና እና ዴምቤሌ ከእሱ እና ቪንሰስ ጁኒየር በተሻለ እንደሚከላከሉ ነግረውት ነበር።

ምባፔ በሰጠው ምላሽ “ እኔም ከጠቀሳችኋቸው ተጨዋቾች በላይ ጎል እንደማገባ መናገር እችላለሁ "ብሏል።

“ እነሱም በዚህ ረገድ መሻሻል እንዳለባቸው ልነግራችሁ እችላለሁ " ሲል ጨምሮ ተናግሯል።

ምባፔ አክሎም “ ሁልጊዜም የአለም ምርጡ ተጨዋች እንደሆንኩ አስባለሁ ” ሲል ተደምጠዋል።

ስለ ባሎን ዶር የተጠየቀው ምባፔ “ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ከሆንክ ስምህ ከዚህ ሽልማት ጋር መያያዙ የተለመደ ነው "ብሏል።

ሰዎች መንገድ ላይ ማሸነፍ አለብህ እያሉኝ ነው የሚለው ምባፔ “ በታላቅ ውድድር ላይ ታሪክ ፅፊያለሁ የሚሆነውን እናያለን “ሲል ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች