ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በፕሪሚየር ሊግ ምን አዲስ ህግ ይኖራል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በፕሪሚየር ሊግ ምን አዲስ ህግ ይኖራል ?
በፕሪሚየር ሊግ ምን አዲስ ህግ ይኖራል ?

በቀጣዩ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዘመን አዲስ የግብ ጠባቂ ህግ እንደሚኖር ተገልጿል።

አዲሱ ህግ ግብ ጠባቂዎች እንደተጎዱ በማስመሰል ጨዋታ እንዳያቋርጡ ለማድረግ በማለም መዘጋጀቱ ተነግሯል።

ለወትሮው ግብ ጠባቂዎች እንደተጎዱ አስመስለው ጨዋታ በማቋረጥ የቡድን አጋሮቻቸው ከአሰልጣኝ ምክር እንዲቀበሉ እድል ይሰጣ።

አለፍ ሲልፍ የቡድን አጋሮቻቸው እረፍት እንዲያገኙ እና ውሃ እንዲጠጡ እንዲሁም ተጋጣሚን ለማዘናጋት ይጠቀሙበታል።

በአዲሱ ህግ ግን ግብ ጠባቂዎች ይህንን ካደረጉ ሌላ አንድ ተጨዋች ለአንድ ደቂቃ ከሜዳ ለመውጣት ይገደዳል።

አሰልጣኙ በአስር ሰከንድ ውስጥ የሚወጣውን ተጨዋች ለአራተኛ ዳኛው የማሳወቅ ግዴታ ይጣልበታል።

አሰልጣኙ በአስር ደቂቃ ውስጥ ካልመረጠ የቡድኑ አምበል ለአንድ ደቂቃ እንዲወጣ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች