ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ታዳጊው ሰላም ነው ከሆስፒታል ወጥቷል ” የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ታዳጊው ሰላም ነው ከሆስፒታል ወጥቷል ” የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት
“ ታዳጊው ሰላም ነው ከሆስፒታል ወጥቷል ” የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት

በሞሮኮ ደጋፊዎች ጥቃት የደረሰበት አልጄሪያዊ ታዳጊ ጤናው መመለሱን የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ቴቦዩን አስታውቀዋል።

አንድ አልጄሪያዊ ታዳጊ ከሞሮኮ እና ኔዘርላንድ ጨዋታ በኋላ አካላዊ ጥቃት ደርሶበት ነበር።

ታዳጊው በአሜሪካ ዳላስ ጨዋታውን ለመመልከት ባመራበት ወቅት በበርካታ ወጣት ሞሮኳዊ ደጋፊዎች ጥቃት ደርሶበታል።

ከጥቃቱ በኋላ ታዳጊው ራሱን ስቶ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ተገልጿል።

የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ቴቦዩ ስለ ጉዳዩ በሰጡት ቃል “ ከአሜሪካ ፖሊስ ጋር በቅርበት እየተከታተልን ነው " ብለዋል።

“ ታዳጊው አሁን ሰላም ነው ከሆስፒታል ወጥቷል " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " ከስዊዘርላንድ በምናደርገው ጨዋታ ስታዲየም ይገኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች