ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አርሰናል ከዩናይትድ ሁለት ታዳጊዎች ሊያስፈርም ነው !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አርሰናል ከዩናይትድ ሁለት ታዳጊዎች ሊያስፈርም ነው !
አርሰናል ከዩናይትድ ሁለት ታዳጊዎች ሊያስፈርም ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከማንችስተር ዩናይትድ ሁለት ታዳጊዎችን ለማስፈረም እየሰራ ይገኛል።

አርሰናል ለማስፈረም እየሰራ የሚገኘው ጄምስ ስካንሎን እና ሀቤብ ኦጉኔዬን መሆኑ ተገልጿል።

የ 19ዓመቱ የክንፍ ተጨዋች ጄምስ ስካንሎን በ 2021 ነበር ከደርቢ ካውንቲ ማንችስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው።

ተጨዋቹ ለእናቱ ሀገር ጂብራልታር 24 ጨዋታዎች ማድረጉ ተገልጿል።

የ 20ዓመቱ ተከላካይ ሀቤብ ኦጉኔዬ በበኩሉ ባለፈው አመት በውሰት በኒውፖርት ካውንቲ አሳልፎ 21 ጨዋታዎች አድርጓል።

መረጃው የ ቴሌግራፍ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች