ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ እኔን እንዲተካ የሾምኩት ሞሪንሆን ነበር ” ፈርጉሰን

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ እኔን እንዲተካ የሾምኩት ሞሪንሆን ነበር ” ፈርጉሰን
“ እኔን እንዲተካ የሾምኩት ሞሪንሆን ነበር ” ፈርጉሰን

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪካዊ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከዚህ በፊት ያልተሰማ ታሪክ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን 2013 ከሀላፊነት ሲለቁ እንዲተኳቸው የተሾሙት ጆዜ ሞሪንሆን እንደነበር ገልጸዋል።

“ ሞሪንሆ እኔን እንዲተካ ጠይቀነው ነበር እኔም ሁሉንም አብራርቼለት ተስማምቶም ነበር “ ሲሉ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በአንዱ ምሽት “ እያለቀሰ ደወለልኝ ” የሚሉት ፈርጉሰን “ ማድረግ አልችልም አሌክስ ለቼልሲ ቃሌን ሰጥቻለሁ ማጠፍ አልፈልግም ሲል ነግሮኛል “ ብለዋል።

አክለውም “ የሰጠኝን ምክንያት ተረድቻለሁ ነገርግን በጣም አበሳጭቶኝ ነበር “ ሲሉ አዲስ በወጣው የጆዜ ሞሪንሆ ዘጋቢ ፊልም ላይ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች