ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ የአሰልጣኝ ክፍሉ እስኪባረሩ ራሴን ከጨዋታ አግልያለሁ “

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ የአሰልጣኝ ክፍሉ እስኪባረሩ ራሴን ከጨዋታ አግልያለሁ “
“ የአሰልጣኝ ክፍሉ እስኪባረሩ ራሴን ከጨዋታ አግልያለሁ “

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ፓፓ ጉዬ በአሰልጣኝ ቡድን አባለቱ ደስተኛ አለመሆኑን ከአሳዛኙ የቤልጅዬም 3ለ2 ሽንፈት በኃላ ተናግሯል።

ተጫዋቹ አሁን ያለው የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እስከሚቀየር ከብሔራዊ ቡድን ራሱን በጊዜያዊነት እንደሚያገል ገልጿል።

በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መልዕክት “ ይህ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እስካለ ድረስ ከዚህ ቡድን ራሴን እንደማገል አስታውቃለሁ “ ሲል ተናግሯል።

ፓፔ ጉዬ አያይዞም ቡድኑ ከውድድር ስለተሰናበተበት ምክንያት “ ስለ ውጤት ማጣታችን ለማናገር እመለሳለሁ “ ብሏል።

ፓፔ ጉዬ በጨዋታው በላሚን ካማራ 6️⃣7️⃣ኛው ደቂቃ ላይ አሰልጣኝ ቲያው ቀይረው አስወጥተውታል።

ስለ ቅያሪው ሲናገር “ በአካል ብቃቱ ጥሩ ነበርኩኝ ፣ ውሳኔው የአሰልጣኙ ነው ፣ ውሳኔውን አከብራላሁ “ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች