ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ዝግጅት ምን ይመስላል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ዝግጅት ምን ይመስላል ?
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ዝግጅት ምን ይመስላል ?

አሰልጣኝ ፓትሪስ ቬይራን በአሰልጣኝነት የሾሙት ሴኔጋሎች ዝግጅታቸውን ከቀናት በኃላ እንደሚጀምሩ ተዘግቧል።

በዛሬው ዕለት አዲሱ አሰልጣኟን በይፋ የምትሾመው ሴኔጋል ከሞዛምቢክ እና ኢትዮጵያ 🇪🇹 ጋር ወሳኝ መርሐ ግብሯን የምታካሂድ ይሆናል።

አሰልጣኝ ፓትሪስ ቬይራ በትላንትናው ዕለት ዳካር ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ሲደርግላቸው “ እዚህ በመገኘቴ ኩራት ይሰማኛል ፣ ቤቴ እገኛለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።

ፓትሪስ ቬይራ አያይዘውም “ ሴኔጋላዊያን በእኔ እምነት ይኑራቸው ፣ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። ሀገሪቷን ለማኩሯት የበኩሌን እወጣለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

የቴራንጋ አምበሶቹ ከቀናት በኃላ ወደ ሞዛምቢክ ማፑቶ በማቅናት ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

ሴኔጋል በሜዳዋ ታደርገው የነበረውን ይህን ጨዋታ በወጣቶች የኦሎምፒክ ዝግጅት ምክንያት ወደ ሞዛምቢክ አቅንታ ለማድረግ ተገዳለች።

ሴኔጋል በአዲሱ አሰልጣኟ እየተመራች ተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችን ስታደርግ:-

• ሴኔጋል ከ ሞዛምቢክ :- መስከረም 15/2019 ዓ.ም ( የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ )

🇪🇹 ኢትዮጵያ ከ ሴኔጋል :- መስከረም 19/2019 ዓ.ም ( የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ )

• ሴኔጋል ከ ኮሞሮስ :- መስከረም 24/2019 ዓ.ም ( የወዳጅነት ጨዋታ ) በፈረንሳይ ማርሴይ ስታድ ቬልድሮም የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች