የዝውውር መስኮቱ ደንብ እንዴት ይሰራል ?

የዝውውር መስኮቱ ደንብ እንዴት ይሰራል ?
ተጨዋቾች አዲስ ክለብ እንዲያገኙ እድል የሚሰጠው የክረምቱ የዝውውር መስኮት በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።
በእንግሊዝ ትላንት ብሔራዊ በዓል መሆኑን ተከትሎ የዝውውር መስኮቱ ዛሬ ሌሊት 7:00 ሰዓት ይዘጋል።
ይህ ህግ የሚያገለግለው የእንግሊዝ ክለቦችን ለሚቀላቀሉ ተጨዋቾች ሲሆን ለሚለቁ ተጨዋቾች የተለየ ሊሆን ይችላል።
ሁሉም ተጨዋቾች በዚህ ጊዜ ውስጥ መመዝገብ ቢገባቸውም ክለቦች የተወሰነ ተጨማሪ ሰዓት ይሰጣቸዋል።
ሊጉ ክለቦች ተጨዋች ለማስፈረም የደረሱትን የስምምነት ሰነድ በማስገባት እንዲያሳውቁ እና ዝውውሩን እንዲያጠናቅቁ እድል ይሰጣል።
ክለቦቹ የስምምነት ሰነዱን ማስገባት የሚችሉት ዋናው የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት መሆኑ ተነግሯል።
ይህንንም ተከትሎ ተጨማሪ የወረቀት ስራዎችን እንዲያጠናቅቁ ሊጉ ተጨማሪ ሰዓት ይፈቅድላቸዋል።
የዘንድሮው የክረምት ዝውውር መስኮት በአምስቱ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ዛሬ በተመሳሳይ ቀን ይዘጋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe