ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሊቨርፑል ተጨማሪ ተጨዋች ሊያስፈርም ይችላል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሊቨርፑል ተጨማሪ ተጨዋች ሊያስፈርም ይችላል ?
ሊቨርፑል ተጨማሪ ተጨዋች ሊያስፈርም ይችላል ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዚህ ሳምንት የብራድሌይ ባርኮላን ዝውውር አጠናቋል።

በሌላ በኩል ኮዲ ጋክፖ በክለቡ መቆየቱ የተጨማሪ ተጨዋች ፊርማ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገልጿል።

ሊቨርፑል በዚህ የዝውውር መስኮት ተጨማሪ የፊት መስመር ተጨዋች ያስፈርማል ተብሎ እንደማይጠበቅ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ሊቨርፑል የ 18ዓመቱን ግብ ጠባቂ ሉካ ብሩህመንስ ከጄንክ በ 33 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ይሁን እንጂ ዛሬ ማማርዳሽቪሊ ክለቡን የማይለቅ ከሆነ በውሰት ወደ ቀድሞ ክለቡ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ክለቡን ማን ሊለቅ ይችላል ?

አሁን ላይ ሊቨርፑልን ለመልቀቅ ከተቃረቡ ተጨዋቾች ውጪ ሌላ ተጨዋች በዚህ ክረምት ላይለቅ እንደሚችል ተነግሯል።

የወደፊት ቆይታው ያልተረጋገጠ ብቸኛው ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬዬሳ መሆኑ ነው የተዘገበው።

መረጃው የ ዘ አትሌቲክ ነው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች