ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ያስፈርማል ?

ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ያስፈርማል ?
ማንችስተር ዩናይትድ ካርሎስ ባሌባ ፣ ቴሌማንስ እና አንድሬ ሳንቶስን በማስፈረም የአማካይ ክፍሉን አጠናክረዋል።
ቀያዮቹ ሰይጣኖች ቀጣይ ትኩረታቸውን በሌሎች የሜዳ ክፍሎች ላይ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ማንችስተር ዩናይትድ የግራ መስመር ተጨዋች ማስፈረም ቀዳሚ ኢላማ ሆኖ ይገኛል።
ስማቸው ከክለቡ ጋር ተያይዞ የነበሩት ሌዊስ ስኬሊ እና ሌዊስ ሀል በሊጉ ለቡድናቸው በቋሚነት ተሰልፈው ሲጫወቱ ነበር።
በተጨማሪም የሁለቱም ተጨዋቾች አሰልጣኞች ተጫዋቾቹ እንደማይለቁ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።
ሌላኛው ኢላማ የባርሴሎናው አሊሀንድሮ ባልዲ ቢሆንም ማንችስተር ዩናይትድ ከፋይናንስ ህግ ጋር በተገናኘ በቋሚነት መግዛት ያስቸግረዋል።
ባርሴሎና በበኩሉ ተጫዋቹን በውሰት ሳይሆን በቋሚነት የመሸጥ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።
ዩናይትድ በተጨማሪም የአስቶን ቪላውን ኢያን ማትሰን እና የሬሲንጉን ጆርጅ ሳሊናስ በአማራጭነት ይዟል።
እንዲሁም ጆሽዋ ዚርኪዜ የሚለቅ ከሆነ አጥቂ በውሰት ሊያስፈርሙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe