ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የደቡብ ኮርያ ህዝብ ተቃውሞ ቀጥሏል !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የደቡብ ኮርያ ህዝብ ተቃውሞ ቀጥሏል !
የደቡብ ኮርያ ህዝብ ተቃውሞ ቀጥሏል !

የደቡብ ኮርያ ህዝብ ብሔራዊ ቡድናቸው በአለም ዋንጫው ከምድብ ማለፍ አለመቻሉን ተከትሎ ተቃውሟቸው ተባብሶ ቀጥሏል።

ቡድኑ በትላንትናው ዕለት ደቡብ ኮርያ ሲደርስ በአሰልጣኙ ሆንጎ ሚዮንግ ቡ ላይ ትልቅ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ባሰሙት ተቃውሞም “ የደቡብ ኮርያ እግር ኳስ ምስጋና ለአንተ ይሁንና 3️⃣0️⃣ዓመት ወደ ኃላ ተመልሷል “ ሲሉ ተሰምተዋል።

ደቡብ ኮርያ ቡድኑ ወደ ሀገሩ ሲመለስ ችግር እንዳይፈጠር ከ 1️⃣6️⃣0️⃣ በላይ የፖሊስ አባለትን በአየር መንገዱ አሰማርታ ነበር።

በሀገሪቱ የሚገኙ የሱቅ ባለቤቶች እና ነጋዴዎች በመገበያያ ቦታዎቻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ በዚህ ቦታ ላይ አሰልጣኝ ሆንጎ ሚዮንግ ቡ መገበያያት አይችልም “ ሲሉ አሳስበዋል።

የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን “ KBS “ ስለ አሰልጣኙ በሰራቸው ዘገባዎች ላይ ፊታቸውን በመሸፈን አየር ላይ ሲያውሉ ታይቷል።

የሀገሪቱ መንግስት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ መግባቱ ሲታወቅ ከሀገሪቱ የስፖርት ሚንስቴር ማብራሪያ መጠየቁ ይታወሳል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች