ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የዲሞክራቲክ ኮንጎ አሰልጣኝ አባት ህልፈተ ህይወት !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የዲሞክራቲክ ኮንጎ አሰልጣኝ አባት ህልፈተ ህይወት !
የዲሞክራቲክ ኮንጎ አሰልጣኝ አባት ህልፈተ ህይወት !

በአለም ዋንጫ በጥሎ ማለፉ በሚያሳዝን ሁኔታ የተሸነፉት ዲሞክራቲክ ኮንጎ አሰልጣኝ ሴባስቲያን ዴሳብሬ ወላጅ አባት ማረፋቸው ተገልጿል።

አሰልጣኙ የወላጃቸውን ህልፈተ ህይወት ትላንት ከጨዋታው በኃላ መስማታቸው ተዘግቧል።

አሰልጣኙ ከጨዋታው በኃላ በነበራቸው የጋዜጣዊ መግለጫ የአባታቸውን ማረፍ በቀጥታ ሰምተዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ የሚዲያ ባለሙያ ሁነቱን ሲያሳውቅ “ አሰልጣኛችን ወላጅ አባታቸውን አጥተዋል ፣ መፅናናትን እንመኛለን “ ሲል በጋዜጠኞች ፊት ሀዘኑን ይፋ አድርጓል።

ድርጊቱን ተከትሎ በርካቶች የአሰልጣኝ ሴባስቲያን ዴሳብሬ ክብር የነካ ድርጊት ነው በማለት ገልፀውታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች