ዩራጓይ ከአሰልጣኟ ጋር ተለያየች !

ዩራጓይ ከአሰልጣኟ ጋር ተለያየች !
በአለም ዋንጫው ደካማ እንቅስቃሴ ያሳየችው ዩራጓይ ከአሰልጣኝ ማርሴሎ ቤይልሳ ጋር መለያየታቸው እውን ሆኗል።
አሰልጣኙ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር መለያየታቸው በይፋ አሳውቀዋል።
ስንብቱን “ የሚያም “ ሲል የገለፁ ሲሆን ተስፋ ያለው የረጅም ጊዜ እቅድ እንደነበራቸው ተናግረዋል።
አሰልጣኙ በሰጡት አስተያየት አለመግባባቶች እንደነበሩ ሲገልፁ በተለይም ተጫዋቾቹ የቤይልሳን የረጅም ደቂቃ የቃል እና የቪድዮ ትንተና አይፈልጉም ነበር።
አሰልጣኙ ይህን ተከትሎ ከግማሽ በላይ ደቂቃዎችን በመቀነስ ከ አስር ደቂቃዎች በታች ቀንሰው እንደነበር ገልፀዋል።
በዚህም ተጫዋቾቹ ደስተኛ አለመሆናቸውን የገለፁት ቤይልሳ “ ሚልዮኖች የሚከፈሉት ተጫዋች ከአስር ደቂቃ በታች ትኩረት ሰጥቶ ለማዳመጥ ፈቃደኛ አለመሆኑ አሳፋሪ ነው “ ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe