ዩናይትድ የዝውውር እቅዱን አይቀይርም !

ዩናይትድ የዝውውር እቅዱን አይቀይርም !
ዩራጓዊው የማንችስተር ዩናይትድ አማካይ ማኑኤል ኡጋርቴ ከባድ ጉዳት እንዳጋጠመው ይታወቃል።
ይህም ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ ክረምት እሱን ለመሸጥ የያዘውን አቅድ እንዳይፈፅም አድርጎታል።
ኡጋርቴ ቢሸጥ በክለቡ ቦታ በመስጠት በፋይናንስ ረገድም ቡድኑ እቅዱን እንዲያሳካ ይረዳው ነበር።
ይሁን እንጂ በኡጋርቴ መጎዳት ምክንያት ማንችስተር ዩናይትድ የያዘውን እቅድ እንደማይቀይር ተገልጿል።
ቀያዮቹ ሰይጣኖች ከወጪ ቅነሳ መርሐ ግብሩ በኋላ በአስተማማኝ የፋይናንስ ቁመና ላይ መሆናቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
የኤደርሰንን ዝውውር ለማጠናቀቅ የተጨዋቹን መመለስ የሚጠበቀው ክለቡ አሁን ትኩረቱ ማቲውስ ፈርናንዴዝ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል የማኑኤል ኡጋርቴ ጉዳት ክለቡ የግራ ክንፍ ተሰላፊ እንዳያስፈርም ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።
በዚህም ምክንያት ማርከስ ራሽፎርድ በክለቡ የሚቀጥልበትን እድል ከፍ እንዳደረገው ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe