ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ዲዮማንዴን ቀጣይ ተከላካይ እናደርገዋለን ”

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ዲዮማንዴን ቀጣይ ተከላካይ እናደርገዋለን ”
“ ዲዮማንዴን ቀጣይ ተከላካይ እናደርገዋለን ”

የሌፕዚጉ የፊት መስመር አጥቂ ያን ድዮማንዴ ስሙ ከሊቨርፑል እና ፒኤስጂ ጋር እያተያያዘ ይገኛል።

ኮትዲቯራዊው አጥቂ ሌፕዚግን የሚለቅ ከሆነ ፒኤስጂ መቀላቀል እንደሚመርጥ እየተዘገበ ይገኛል።

ይሁን እንጂ ፒኤስጂ ተጫዋቹን ለማስፈረም እስካሁን ይፋዊ እንቅስቃሴ አላደረገም።

የሌፕዚግ የስፖርት ዳይሬክተር ማርሴል ሼፈር በበኩላቸው ተጫዋቹ ሊለቅ ነው መባሉን ውድቅ በማድረግ “ ለሽያጭ አይቀርብም “ ብለዋል።

“ ሀሳባችን ዲዮማንዴ በሚቀጥለው አመት የቀኝ መስመር ተከላካይ ሆኖ እንዲጫወት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ተጨዋቹ በዚሁ ከቀጠለ አዲስ ነገር እንዲሞክር አድል እንሰጠዋለን ነገርግን በዚህ አመት አይደለም " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች