ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#Ethiopia 🇪🇹

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#Ethiopia 🇪🇹
#Ethiopia 🇪🇹

የአዲስ አበባ ሯጮች በምስራቅ አፍሪካ ዩጋንዳ ላይ በሚካሄድ የማራቶን ውድድር እንዲሳተፉ ግብዣ ቀረበ።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ከዩጋንዳው ተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን ጋር በመተባበር ለሩጫ ወዳጆች ጥሪ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ የምስራቅ አፍሪካን ተራራማ መልከዓ ምድር ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን የሩጫ ውድድር ወደ ታላቅ በዓል የመቀየር ተመሳሳይ ባህል አላቸው።

ሰኔ 27/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ፣ እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ እና ሌሎችም የሩጫ አፍቃሪያን ከሀገር ውጪ በመጓዝ ውድድሩን እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል።

ተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ባለባት በዩጋንዳ ካሲሴ ከተማ ይካሄዳል።

የተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን የዓለም አትሌቲክስ ሌብል ደረጃ ሲኖረው ያለው የአትሌቶች ጥራት እና አደረጃጀት በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ 200 ውድድሮች አንዱ ያደርገዋል።

በውድድሩ ከማራቶን በተጨማሪ በ5 ከ.ሜ.፣ 10 ኪ.ሜ.፣ እና 21 ከ.ሜ . (ግማሽ ማራቶን) መሳተፍ ይችላሉ።

የሩጫው መስመር በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ በሆነው የንግስት ኤልሳቤጥ ብሔራዊ ፓርክ ይጀምራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች