ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#LionelMessi

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#LionelMessi
#LionelMessi

ሌሊት በተደረገ የሜጀር ሊግ ሶከር ጨዋታ ኢንተር ሚያሚ ከሳን ዲያጎ እግር ኳስ ክለብ ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል::

ሊዮኔል ሜሲ እና ሉዊስ ሱዋሬዝ የኢንተር ሚያሚን ጎሎች አስቆጥረዋል::

የሳን ዲያጎው አጥቂ ድሬየር በበኩሉ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ቡድኑ ነጥብ እንዲጋራ አድርጓል::

ሊዮኔል ሜሲ በጨዋታው ላይ ያስቆጠረው ግብ በእግር ኳስ ዘመኑ 75ኛ የቅጣት ምት ጎሉ ሆኖ ተመዝግቧል::

ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ዘመኑ 9️⃣3️⃣0️⃣ኛ ጎሉን እንዲሁም ለ ኢንተር ሚያሚ 1️⃣0️⃣1️⃣ኛ ግቡ ላይ ደርሷል።

ኢንተር ሚያሚ ካለፉት ዘጠኝ የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው::

በተከታታይ አራት የሊጉ ጨዋታዎችም ኢንተር ሚያሚ የአቻ ውጤት አስመዝግቧል::

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ወደ 3️⃣ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች