በኢሮብ ወረዳ 35 ሺህ ህዝብ ለከባድ ድርቅ ተጋልጧል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

በኢሮብ ወረዳ 35 ሺህ ህዝብ ለከባድ ድርቅ ተጋልጧል።
በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚገኘው ኢሮብ ወረዳ ከባድ ድርቅ እየተጋፈጠ ሲሆን በአካባቢው የሚኖሩ 35 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለድርቅ አደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።
በወረዳው የክረምት ዝናብ በበቂ ሁኔታ ባለመዝነቡ የውሃ ጉድጓዶች መድረቃቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በውሃ እጥረቱም የቤት እንስሳት መሞት መጀመራቸውን አስረድተዋል።
በወረዳው የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በከፍተኛ ተራራና ተዳፋት አካባቢዎች መሆናቸው የተጀመረውን የእርዳታ ማዳረስ ስራ ፈታኝ እንዳደረገው ተጠቁሟል።
የአካባቢው አርሶ አደሮች እንደሚሉት፣ ከዚህ በፊት እንደ ዘንድሮ ያለ ከባድ ድርቅ አጋጥሟቸው አያውቅም።
የዝናብ እጥረቱ በማሳ ላይ የተዘራው እህል እንዲደርቅ ከማድረጉም በላይ በክረምት ዝናብ ይሞሉ የነበሩ የውሃ ጉድጓዶች እንዲደርቁ አድርጓል።
የኢሮብ አካባቢ የኢሮብ ብሄረሰብ የሚኖርበት ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች አንዱ ነው። አካባቢው በ2013 ዓ.ም. በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ ጥቃት የደረሰበት ሲሆን እስካሁንም አንዳንድ የቀበሌ ገበሬ ማህበራት በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።
የድርቁ አደጋ በሰዎችና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት ለጋሽ ድርጅቶች፣ ባለሀብቶችና ግለሰቦች የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ወረዳው ቀደም ሲል ጥሪ አቅርቧል።
በዚህ ጥሪ መሰረት አንዳንድ ግለሰቦች የእርዳታ እህል ማቅረብ መጀመራቸው ተገልጿል። ሆኖም የእንስሳት መኖ፣ የሰዎችና የእንስሳት መጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት አሁንም የድርቁን ተጽዕኖ ለመቀነስ የሚደረገውን ስራ ከባድ እያደረገው እንደሆነ ተጠቁሟል።
የአካባቢው ህዝብ የውሃ፣ የምግብ እና የእንስሳት መኖ አቅርቦት በአስቸኳይ እንዲጠናከር ጥሪ እያቀረበ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia