ቪድዮ ፦ ሮቦቶች በድንገት ሰዎችን ሊያጠቁ ይችላሉ ? በሩሲያና ቻይና የተከሰቱ ክስተቶች ጥያቄ አስነሱ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·
ቪድዮ ፦ ሮቦቶች በድንገት ሰዎችን ሊያጠቁ ይችላሉ ? በሩሲያና ቻይና የተከሰቱ ክስተቶች ጥያቄ አስነሱ።
በሩሲያ ሳራቶቭ ከተማ በሚገኝ የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ “Syoma” የተባለ ሮቦት አንድ ደንበኛን ለማጥቃት ሲሞክር የሚያሳይ የደህንነት ካሜራ ቪዲዮ ከሰሞኑ ተሰራጭቶ መነጋገሪያ ሆኗል።
ቪዲዮው ላይ ደንበኛው ሮቦቱን ከገፋው በኋላ፣ ሮቦቱ ወደ እሱ በመሄድ በእግሩ ለመርገጥና ለመደባደብ ሲሞክር ይታያል። ደንበኛው በፍጥነት ከቦታው ሲሸሽ የሱቁ ሰራተኞች ሮቦቱን አስቁመዋል። በኋላም ሮቦቱ እንደገና እንዲነሳ (reboot) ተደርጓል።
በሩሲያው ክስተት ላይ ሮቦቱ ለምን በዚህ መንገድ ምላሽ እንደሰጠ የቴክኒክ ስህተት፣ የስርዓት ችግር፣ የቁጥጥር ችግር ወይም ሌላ ምክንያት በግልጽ አልታወቀም።
ተመሳሳይ የሚመስል ክስተት በቻይና ዜጂያንግ ግዛትም ተመዝግቧል። የደህንነት ካሜራ ቪዲዮ እንደሚያሳየው፣ አንድ ሮቦት የሰራውን መሐንዲስ ሊያጠቃ ሲሞክር ታይቷል።
በቪዲዮው ላይ ሮቦቱ መሬት ላይ ተንበርክኮ ወደነበረው መሐንዲስ በመሄድ፣ በእጁ የያዘውን የርቀት መቆጣጠሪያ በእግሩ መትቶ ሲጥለው ይታያል። ሮቦቱ ያደረገው ድንገተኛ እንቅስቃሴ ምን እንዳስከተለው ግን ጥያቄ አስነስቷል።
ሁለቱ ክስተቶች የAIና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂዎች የበለጠ ራሳቸውን ችለው እየሰሩ በሚሄዱበት ወቅት፣ ሮቦቶች ባልተጠበቀ መንገድ እርምጃ ቢወስዱና ጉዳት ቢያደርሱ ለዚያ ድርጊት ተጠያቂው ማን ይሆናል ? የሚል ጥያቄ አስነስተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአርቲ እና ዴይሊሜል ነው ያገኘው።
መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia