" ከ90 በመቶ በላይ የሕክምና ተማሪዎች በሚያገኙት ሥልጠና ደስተኛ አይደሉም " - የዓለም ባንክ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ከ90 በመቶ በላይ የሕክምና ተማሪዎች በሚያገኙት ሥልጠና ደስተኛ አይደሉም " - የዓለም ባንክ
በኢትዮጵያ ከ9ዐ በመቶ በላይ የሕክምና ተማሪዎች በሚያገኙት ሥልጠና እርካታ እንደማይሰማቸው መግለጻቸውን፣ የዓለም ባንክ በሪፖርቱ አመላከተ።
የዓለም ባንክ ተማሪዎቹ ደስተኛ አለመሆናቸውን ያስታወቀው የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸምና ብልፅግና (Public Workforce Performance and Prosperity) በሚል ርዕስ ባሳተመው፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞችን ፦
- ብዛትና የዘርፍ ክፍፍል፣
- የደመወዝ ክፍያ አወቃቀር፣
- የምልመላና የቅጥር ሥርዓት፣
- የሥራ አፈጻጸም አመራርና ሥልጠና፣
- የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የመንግሥት ሠራተኞች ብቃትና የሥራ ተነሳሽነት የሚመለከቱ ጉዳዮችን በዳሰሰበት ሪፖርቱ ነው።
ሪፖርቱ በተለይ የመንግሥት የደመወዝ ወጪ፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ልምዶችና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እንደ ዋና የሠራተኛው የሥራ አፈጻጸም መመዘኛዎች ወስዶ በመመርመር፣ የጤናና የትምህርት ሠራተኞችን ጨምሮ የመንግሥት ሠራተኞች ብቃትና የሕዝብ አገልግሎት አፈጻጸምን ይመረምራል።
በኢትዮጵያ ግምገማ ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ በሆነው የጤና ዘርፍ ክፍልን የተመለከተ በዝርዝር ዳሰሳ ያደረገ ሲሆን፣ ከግኝቶቹ መካከልም ሪፖርቱ የመንግሥት የሕክምና ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ቅበላ ከሦስት እስከ አራት እጥፍ እንዲያሳድጉ ካደረገ በኋላ የተከሰተው ፈጣን የሕክምና ትምህርት መስፋፋት ከተቋማቱ አቅም በላይ እንደሆነ አመልክቷል።
ሪፖርቱ በዚህም ምክንያት ሕክምና እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች 9ዐ በመቶ የጥራት ክፍተቶች በመኖራቸው ተመራቂዎች በቀጥታ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡበት የሥራ መስክ በቂ ዝግጅት ሳይኖራቸው እንዲወጡ እያደረገ መሆኑን ገልጸው እያገኙ ባሉት የትምህርት ሥልጠና እርካታ እንደማይሰማቸው አሳውቀዋል ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ነባር የመንግሥት የሕክምና ትምህርት ቤቶች የሚቀበሏቸውን ተማሪዎች ብዛት ከሦስት እስከ አራት እጥፍ እንዲያሳድጉ ሲያደርግ፣ የተማሪ ብዛት የተቋማቱን አቅም መብለጡንና ከ90 በመቶ በላይ ተማሪዎች በሚያገኙት ሥልጠና እንዳልረኩ መግለጻቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል።
ሪፖርቱ ይህ ግኝት በሕክምና ትምህርት ዘርፍ ያሉ የጥራት ክፍተቶችን የሚያሳይ መሆኑን ጠቁሞ፣ እነዚህ ክፍተቶች ተመራቂዎች በቀጥታ የጤና አገልግሎት ለሚሰጡበት የሥራ መስክ በቂ ዝግጅት ሳይኖራቸው እንዲወጡ የሚያደርጉ መሆናቸውን፣ በኋላ የሚደረጉ የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓቶች ላይም ተጨማሪ ጫና እንደሚፈጥሩ ጠቁሟል።
ሪፖርቱ በተለይም ተማሪዎች በሥራ ላይ ከመሰማራታቸው በፊት የሚሰጥ ሥልጠና፣ እንዲሁም የፈቃድና የዕውቅና ሥርዓቶች (licensing and accreditation systems) ደካማ በሆኑባቸው አገሮች በብቃት ላይ የተመሠረተ ቅጥር አስፈለጊ መሆኑን አሳስቧል።
አያይዞም የኢትዮጵያን ብሔራዊ የሙያ ብቃት ማረጋገጫና ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት እያደገ ያለውን የጤና ሠራተኛ ኃይል በብቃት ለማስተዳደር የሚያስችለው አቅምና የቴክኖሎጂ ሀብት እንደሌለው፣ እንዲሁም ሥርዓቱ አብዛኛውን ጊዜ ከተግባራዊ ብቃት ይልቅ ለንድፈ ሐሳብ ዕውቀት ቅድሚያ እንደሚሰጥ አመላክቷል።
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓቶች በቂና ጠንካራ ባልሆኑበት ሁኔታ፣ ብቃት ያላቸውና በቂ የትምህርት ዝግጅት ያደረጉ ግለሰቦች በወሳኝ ሥራዎች ላይ መመደባቸውን ለማረጋገጥ የቅጥር ሒደቱ የመጨረሻ የብቃት ማጣሪያ ሊሆን እንደሚገባ ሪፖርቱ ገልጿል።
ዓለም ባንክ በሪፖርቱ ሌላኛው ክፍል በአገሪቱ የመንግሥት ሠራተኞች የሚቀጠሩበትን መንገድ የዳሰሰ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ወደ 30 በመቶ የሚጠጉ የመንግሥት ሠራተኞች በውድድር ሒደት ሳያልፉ ወደ ሥራ መግባታቸውን አውስቷል።
ሪፖርቱ ብቃትን መሠረት ያደረገና በግልጽነት የሚመራ የቅጥር ምልመላ መኖር፣ የመንግሥት የሠራተኛ ኃይል ጥራት ያለው እንዲሆን ለማስቻል ወሳኝ ነው ያለ ሲሆን፣ አያይዞም የመንግሥት ሠራተኞች በአጠቃላይ ለረዥም ጊዜ በሥራ ላይ የሚቆዩ በመሆናቸው፣ የሥራ ቅጥር ለሁሉም ክፍት የሆነና ውድድር ያለበት የምልመላ ሒደት ሊኖረው እንደሚገባ ገልጿል።
ሆኖም ለሁሉም ክፍት የሆነ የቅጥር ውድድር ያለበት ደረጃ ግን በተለያዩ አገሮች ከሚጠበቀው ደረጃ በታች መሆኑን ጠቁሟል።
ኢትዮጵያን ከአርሜኒያና ከኡራጓይ ጋር በማሠለፍ በሦስቱም አገሮች ወደ 30 በመቶ የሚጠጉ የመንግሥት ሠራተኞች ክፍት በሆነ የቅጥር ውድድር ሒደት ሳያልፉ፣ በመንግሥት ሠራተኝነት መቀጠራቸውን አስታውቋል፡፡
ሪፖርቱ የምልመላ ሒደት ጥራት ከመንግሥት የሠራተኛ ኃይል ብቃት ጋር የሚያያዝ መሆኑን ጠቅሶ፣ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ አገሮች የመንግሥት ተቋማት በቂ ሠራተኛ እንደሌላቸውና ያሉትም ሠራተኞች የብቃት ማነስ እንዳለባቸው ገልጿል።
የምልመላ ሒደት ብቃትን መሠረት ባደረገ መንገድና በግልጽነት አለመመራት፣ ለሠራተኞች ብቃት ማነስ አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ነገሮች መካከል መሆኑን አስረድቷል፡፡
የዓለም ባንክ ከመንግሥት ሠራተኞች ባሻገር ተቋማት ላይ ባደረገው ግምገማ በኢትዮጵያ 29 በመቶ የሚሆኑ የተቋማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊዎች፣ በጤናና በትምህርት ተቋማት የሚያደርጉት ቁጥጥር በዓመቱ ከሁለት ጊዜ በላይ እንደማይሆን መግለጻቸውንም አክሏል።
ሪፖርቱ የመስክ ጉብኝቶች ለአገልግሎት ሰጪዎች ግብረ መልስና መመርያ ለመስጠት፣ እንዲሁም ችግሮችን በጋራ ለመፍታት በተለይም ሩቅና አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ለሚሠሩ የአገልግሎት ሰጪዎች የሥራ ተነሳሽነትን ለማሻሻል የሚያግዙ ቢሆንም ግምገማ በተደረገባቸው በርካታ አገሮች የመስክ ጉብኝቶች በተደጋጋሚ እንደማይከናወኑና የቁጥጥር ሒደት አሠራር ጥራት ዝቅተኛ መሆኑን ገልጿል።
የቁጥጥርና ክትትል ጉዳይን በተመለከተ በኢትዮጵያ ባደረገው ጥናት 29 በመቶ የሚሆኑ የአስተዳደር ኃላፊዎች፣ በጤናና በትምህርት ተቋማት ላይ የሚያደርጉት ክትትልና ቁጥጥር በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ እንደማያልፍ መጠቆማቸውን አስረድቷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia