ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ መጥታችሁ የራሳችሁን ንብረት በመለከት መረከብ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ መጥታችሁ የራሳችሁን ንብረት በመለከት መረከብ ትችላላችሁ " - ፖሊስ
" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ መጥታችሁ የራሳችሁን ንብረት በመለከት መረከብ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተሽከርካሪ እቃዎችን በመስረቅ የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦችንና የተሰረቁ እቃዎችን ይገዙ የነበሩ 2 ተቀባዮችን በድምሩ 7 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለጸ።

ፖሊስ በክፍለ ከተማው በተበራከተው የመኪና እቃ ስርቆት ላይ የተመሠረተ ክትትል ሲያደርግ ከቆየ በኋላ፣ ለአንድ ወር ከ15 ቀን በተካሄደ ምርመራ ተጠርጣሪዎቹን መያዙን ገልጿል።

ፖሊስ በበቂ ማስረጃ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል ብሎ የጠረጠራቸው 5 ግለሰቦች ፦
° ዳዊት መንግስቱ፣
° ከድር አህመድ፣
° ማሃዲ ሳቢት፣
° ኤሊያስ አረጋ እና በቃሉ አንዱዓለም ናቸው።

ደረጀ ታደሰ እና ቾምቤ ሀይሉ የተባሉት ሁለት ግለሰቦች ደግሞ የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን ሲገዙ እንደነበር በመረጋገጡ መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ቀናትና ቦታዎች ከሌሊቱ 7 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ባለው ጊዜ የመኪና እቃዎችን ሲሰርቁ እንደነበር ምርመራው ማረጋገጡንም አስታውቋል።

በሸገር ሲቲ መልካ ኖኖ ወረዳ፣ አንፎ በሚባል አካባቢ የተሰረቁ የመኪና እቃዎች በሚቀበሉት ግለሰቦች ሱቅ ላይ በሕግ አግባብ በተደረገ ፍተሻ፦-
- የተሽከርካሪ ጌጅ
- ስፖኪዮ
- ዳሽቦርድ
- ፎቶ ኮፒ ማሽን
- ኮምፒውተር
- ሶስት (3) ህገወጥ ሽጉጦችና 2 ጥይቶች
- መቁረጫ መሣሪያዎች
- ኮድ 2 አ/አ 40817 የሆነ ዴኤክስ ተሽከርካሪ
- ኮድ 3 አ/አ 96821 የሆነ ፕላትስ ተሽከርካሪ ... ተገኝተዋል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ መጀመሪያ 11 የምርመራ መዝገቦች የተደራጁ ሲሆን፣ ምርመራው ወደ ቦሌ፣ ለሚ ኩራ፣ የካ፣ አቃቂ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ተስፋፍቶ 10 ተጨማሪ መዝገቦች ተደራጅተዋል።

በድምሩ 21 የምርመራ መዝገቦች የተያዙ ሲሆን፣ ክስ ለመመሥረት ሂደት ላይ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ይስተዋል የነበረው የመኪና እቃ ስርቆት በእጅጉ መቀነሱን አስታውቋል።

እቃዎቻቸው የተሰረቁባቸው ዜጎችም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ዋና ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ የተያዙትን እቃዎች መለየትና የራሳቸውን ንብረት መርጠው መረከብ እንደሚችሉ ፖሊስ ገልጿል።

ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች