ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የበዓል ዝግጅት

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የበዓል ዝግጅት
የበዓል ዝግጅት

የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ለመጪዎቹ የአዲስ ዓመት፣ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት የምርት አቅርቦት እንዳይጎድል ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሽታዬ ሙሐመድ እንዳስታወቁት፣ ለበዓላቱ የሚያስፈልጉ ጤፍ፣ ነጭ ዱቄት፣ ዘይት፣ እንቁላል፣ ዶሮና ሌሎች መሠረታዊ ምርቶች በበቂ ሁኔታ እንዲቀርቡ ከዩኒየኖች፣ ከሸማች ማህበራትና ከአምራች አካላት ጋር ሥራ እየተሰራ ነው።

በተለይ የሽንኩርት አቅርቦትን በተመለከተ፣ ከክልሎች ካሉ ዩኒየኖች ጋር ትስስር በመፍጠር ምርቱን ወደ አዲስ አበባ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽነሯ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በሸማች ማህበራት የሚቀርበው ሽንኩርት ከ60 እስከ 65 ብር አካባቢ እንደሚሸጥ ጠቁመዋል።

ሽንኩርት ላይ በክረምት ወቅት የዋጋ ጭማሪ፣ በበጋ ደግሞ የዋጋ ቅናሽ የመኖር ዝንባሌ እንዳለ የገለጹት ኮሚሽነሯ፣ በእጥረት ወቅት የሚከሰቱ የአቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ የገበያ አማራጮችን ማስፋት ላይ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

የዘይት አቅርቦትን በተመለከተ በዩኒየኖች በኩል በየቀኑ ከ2 ሺህ እስከ 4 ሺህ ካርቶን ዘይት ወደ ሸማች ማህበራት እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል።

ምርቶቹ ለህብረተሰቡ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በሚዘጋጁ ባዛሮች፣ በ700 በላይ የሸማች ሱቆች እና 154 መሠረታዊ የሸማች ማህበራት በኩል እንደሚቀርቡ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በስጋ አቅርቦት በኩልም የበዓላቱን ፍላጎት ለመሸፈን 274 የስጋ ቤቶች ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ በአጠቃላይ በበዓላቱ ወቅት የምርት እጥረት እንዳይከሰትና ህብረተሰቡ መሠረታዊ ምርቶችን በተሻለ ሁኔታ እንዲያገኝ አቅርቦትና ስርጭትን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች