የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶች የአተገባበር ማንዋል ይፋ አድርጓል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶች የአተገባበር ማንዋል ይፋ አድርጓል።
👉 በመተግበሪያ ማንዋሉ መሰረት አንድ ተማሪ ከአቅሙና ከፍላጎቱ ጋር የተያያዘ አንድ የሙያ ዓይነት ብቻ መርጦ የሚማር ሲሆን፣ ትምህርት ቤቶች ሁሉንም 11 ዓይነት ሙያዎች በአንድ ጊዜ እንዲተገብሩ አይገደዱም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እና ተማሪዎችን ለሥራው ዓለም ለማዘጋጀት ያለመ አዲስ የአተገባበር ማንዋል አዘጋጅቷል።
በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ማንዋል፣ በ2019 ዓ.ም በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶች ትግበራ የሚውል ሲሆን፤ የትምህርቱን አስፈላጊነት፣ ዓላማ፣ የአመራረጥ ሂደት እና የተግባርና ኃላፊነት ክፍፍልን በዝርዝር አካቷል።
ቢሮው በመመሪያው መግቢያ ላይ እንደገለጸው፣ ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ሚና ቢኖረውም፣ በተካሄደው የፍኖተ ካርታ ጥናት መሰረት የአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱ ከሥራና ተግባር ጋር ያልተሳሰረና የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎትን ያላካተተ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ ችግር ተማሪዎችን በመሠረታዊ እውቀት ብቻ ያቆምና በሥራ ዓለም ተግባራዊ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የማያስችል ነው ይላል።
ችግሩን ለመፍታትም በ2017 እና 2018 ዓ.ም በሁለተኛ ደረጃ ላይ በሚገኙ ተማሪዎች በስምንት የሙያ መስኮች ማለትም ፦
- በግብርና ፣
- መረጃ ቴክኖሎጂና ኮምፒውተር ሳይንስ ፣
- ጤና ሳይንስ፣
- ኮንስትራክሽን፣
- ማኑፋክቸሪንግ ፣
- ኮሙኒኬሽንና የማህበራዊ ሳይንስ ፣
- ቢዝነስ ሳይንስ እና ስነጥበባት ውስጥ ከሚገኙት የሥራ አይነቶች አንዱን መርጠው እንዲማሩ መደረጉን አስታውሷል።
ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮም ከዕድሜ ጋር የተመጣጠነ የሥራና ተግባር ትምህርት እንደተሰጠ የአተገባበር መመሪያው ያስረዳል።
አሁን ደግሞ በ2019 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚቀርቡ 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤቱ እና በተማሪው ምርጫ ተግባራዊ ለማድረግ የመተግበሪያ መመሪያ (Manual) መዘጋጀቱ አመልክቷል።
በዚህ አዲስ የአተገባበር ሥርዓት ውስጥ የተካተቱት 11 የሙያ ዓይነቶች በስድስት ዋና ዋና የሙያ ዘርፎች (Career Clusters) የተከፋፈሉ ናቸው።
° በግንባታ ዘርፍ የሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና የቧንቧ ስራ፤
° በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የብረታ ብረት ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ እና አልባሳት ቴክኖሎጂ ፤
° በቢዝነስ ሳይንስ ዘርፍ የሆቴል አገልግሎት፣ የፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እንዲሁም የምግብ ዝግጅት ተካተዋል።
በተጨማሪም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሶፍትዌር ማበልጸግ፣ በግብርና ሳይንስ የሰብል አመራረት እና በጤና ሳይንስ የጤና ክብካቤ አገልግሎት የሙያ ዓይነቶች ለተማሪዎች እንዲቀርቡ ተለይተዋል።
የሙያ ዓይነቶቹ የሚመረጡበት ሂደት ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን በመመሪያው ታዟል።
ትምህርት ቤቶች የሙያ ዓይነቶችን ከመምረጣቸው በፊት የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ ያሉትን የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ግብዓቶች፣ እንዲሁም የተማሪዎችን ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በአተገባበር በመመሪያው መሠረት አንድ ትምህርት ቤት ሁሉንም 11 የሙያ ዓይነቶች ማቅረብ አይጠበቅበትም፤ ይልቁንም እንደ አቅሙና እንደ አካባቢው ሁኔታ የተወሰኑትን መርጦ ተግባራዊ ያደርጋል።
ተማሪዎችም ከቀረቡት አማራጮች መካከል የአንዱ የሙያ ዓይነት ባለቤት እንዲሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ምርጫቸውም ከፍላጎታቸውና ከችሎታቸው ጋር የተገናኘ መሆን እንዳለበት ተደንግጓል።
ለመመሪያው መሳካት የተለያዩ አካላት የየራሳቸው ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የመሪ ዕቅድ የማዘጋጀትና ክትትል የማድረግ ኃላፊነት ሲኖርበት፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ደግሞ ትምህርት ቤቶች የሙያ ዓይነቶችን እንዲለዩ ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ሙያውን የሚከታተሉ ባለሙያዎችንም ይመድባሉ።
ትምህርት ቤቶች በበኩላቸው ካሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር የሙያ ዓይነቶችን የመምረጥ፣ ለተማሪዎች ግንዛቤ የመፍጠርና ትግበራውን የመምራት ቀጥተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ይህ የሥራና ተግባር ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ትምህርት ቤቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከግል ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው መተግበሪያ መመሪያው ያሳስባል።
ይህም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ሥራ ፈጣሪ ዜጎች እንዲሆኑና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ቢሮው ለትግበራው ምቾት ይረዳ ዘንድ ለትምህርት ቤቶችና ለተማሪዎች ምርጫ የሚሆኑ ቅጾችንም ከመመሪያው ጋር አያይዞ አቅርቧል።
ሙሉ የአተገባበር ማንዋሉን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia