ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና ኤክስፖርተር የሆነው "ሔሌፍ ቡና/Heleph Coffee" ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ ተቀላቀለ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና ኤክስፖርተር የሆነው "ሔሌፍ ቡና/Heleph Coffee" ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ ተቀላቀለ።
የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና ኤክስፖርተር የሆነ "ሔሌፍ ቡና/Heleph Coffee" ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ ተቀላቀለ።

የኢትዮጵያን ስፔሻሊቲ ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ "ሔሌፍ ቡና - Heleph Coffee በሀገር ውስጥ ጥራት ያለው ስፔሻሊቲ የቡና ምርት ለማቅረብ በእህት ኩባንያዉ በሰቨን ትረስት ግሩፕ አማካኝነት የሀገር ውስጥ የሽያጭ ስራ መጀመሩን አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. ከ2018 ጀምሮ ወደ ጃፓን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አሜሪካ እና አዉሮፓን ጨምሮ በበርካታ የዓለም ሀገራት የኢትዮጵያን ቡና በኤክስፖርት ሲያስተዋውቅ የቆየው ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የላቀ ጥራት ያለው የስፔሻሊቲ ቡናን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ማቅረብ ጀምሯል።

በተጨማሪም ግሩም ጣዕምና መዓዛ ያለው ሔሌፍ ቡና በሀገር ውስጥ ብዙ ባልተለመደው "ድሪፕ ኮፊ"  እንዲሁም በ500 ግራም ፓኬጅ ነው ምርቱን ያቀረበው።

የሰቨን ትረስት ግሩፕ አስተዳደር እንደገለጸው የምርቱ ጥራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካገኙ የኤክስፖርት ምርቶች ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ያለው ነው።

ኩባንያው ከቡና እርሻ ቦታዎች ጋር በቀጥታ በመስራትና በጥራት ላይ የተመሰረተ አሰራርን በመከተል ቀደም ሲል ለኤክስፖርት ብቻ ይውሉ የነበሩ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ሸማቾች በዘላቂነት በማቅረብ ረገድ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።

ይህ እንቅስቃሴ ጥራት ያለው ቡናን ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ተደራሽ ከማድረጉም በላይ በአካባቢው የቡና ባህል ላይ አዎንታዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ከገበሬዎች ጋር በቀጥታ በመስራት የቡናውን ጥራት ከእርሻ እስከ ሸማቹ ድረስ የሚጠብቅ ጥብቅ ስርዓት እንደሚከተል የገለጸው ኩባንያው፣ የእርሻ ቦታዎቹ ባሉባቸው እና በሌሎችም አካባቢዎች ማህበረሰቦችን በመደገፍና ሴቶችን በግብርና ማብቃት እሴቶቹ አድርጎ እየሰራ ነው።

አድራሻ፦
አዲስ አበባ
ከቦሌ ወደ መገናኛ በሚወስደዉ መንገድ ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ እንዳለፉ ወደ ግራ ታጥፈው 100 መቶ ሜትር ገባ ብሎ።
በተጨማሪም በስልክ +251116394432/  ያገኙናል።

ምርቶችን ለማግኘት እና አብሮ በጋራ ለመስራት @helephcoffee / @helephcoffee_BOT ይጠቀሙ።

#HelephCoffee X #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች