የፌዴሬሽን ም/ቤት የጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን ኢ-ሕገመንግሥታዊ ሲል ሻረ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የፌዴሬሽን ም/ቤት የጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን ኢ-ሕገመንግሥታዊ ሲል ሻረ
👉 " በሌላ ሰው መሬት ላይ የተገነባ ቤት የመሬቱን ባለይዞታ ባለቤት አያደርግም። "
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ናቸው ሲል ሽሯቸዋል።
በዚህም መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሠራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል" በማለት በመዝገብ ቁጥር 30101 እና 36638 ላይ የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረኑ ናቸው በማለት ውድቅ አድርጎታል።
የምክር ቤቱ ውሳኔ እንደሚያመላክተው፤ በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ የመሆን እና በመሬቱ የመጠቀም ሕገ-መንግሥታዊ መብቱ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው።
በዚህም መሠረት አንድ ሰው የሌላ ሕጋዊ ባለይዞታ በሆነ መሬት ላይ፥ ባለይዞታው ሳይቃወመው እንኳን ቢገነባ የመሬቱ ባለይዞታነትም ሆነ የቤቱ ሙሉ ባለሃብትነት ወደ ቤቱ ሠሪ አይተላለፍም።
የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) "በመሬት ላይ ንብረት ያፈራ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ የሚሠራው ሕጋዊ የመሬት ባለይዞታነት መብት ላለው አካል እንጂ፣ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለ ሕጋዊ መሠረት ንብረት ለገነባ ሰው የቤት ባለቤትነት መብት ለመስጠት እንዳልሆነ ምክር ቤቱ አብራርቷል።
በመሆኑም ባለይዞታው ሳይቃወም በይዞታው ላይ ቤት የሠራ ሰው የሚኖረው ሕገ-መንግሥታዊ መብት፣ ለግንባታው ያወጣውን ወጪ ወይም ግምት ከመሬቱ ባለይዞታ የመጠየቅ መብት ብቻ መሆኑ ተጠቅሷል።
ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
Via @tikvahethmagazine