" ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው። አዲስ ሀዘን ነው የሆነብን ! " - የዘውዱ ሃፍቱ እህት
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው። አዲስ ሀዘን ነው የሆነብን ! " - የዘውዱ ሃፍቱ እህት
ከሁለት ዓመት በፊት በመቐለ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በነበረችው ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተጠርጥረው እድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ሁለት ፍርደኞች በነጻ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ቢቢሲ አማርኛ የሟች ቤተሰብን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
የመቐለ መካከለኛ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ያሬድ ገብረስላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያምን " ነጻ ናቸው " ብሏቸዋል።
ውሳኔው የተላለፈው ለታችኛው ፍርድ ቤት በማስረጃነት ቀርቦ የነበረ ዲጅታል ሰነድ ከፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት በመጥፋቱ መሆኑን የዘውዱ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
ይህ ወሳኝ ዲጅታል ማስረጃ ያሬድ የተባለው ፍርደኛ ይዞት ከነበረው ሲም ካርድ ጋር የተያያዘ ነው።
ዘውዱ ነሃሴ 13/2015 የአሸንዳ በዓል ለመታደም ተዘጋጅታና የጓደኛዋን ልደት ለማክበር ከቤት በወጣችበት ' አዲሃውሲ ' በተባለ ቦታ ምሽት ላይ ተገድላ አስክሬኗ በመኪና ተጎትቶ መንገድ ላይ ተጥሎ ነው የተገኘው።
በዚህ ዘግናኝና አስደንጋጭ ግድያ ምክንያት መሪር ሃዘን ውስጥ የገቡት የሟች አባት ህይወታቸው አልፏል።
ፍርደኞቹ " ነጻ " ስለተባሉበት የዛሬው ችሎት የሟች ታናሽ እህት ብርቱካን ሃፍቱ ለቢቢሲ አማርኛ ምን አለች ?
" ተከሳሾች መጀመሪያ ወደ ክልል ፍርድ ቤት ነው ይግባኝ ያሉት ክልል ፍርድ ቤት መዝገቡን አይቶ የተፈረደው ፍርድ ትክክል ነው ብሏል።
ከዛ ግን ሰበር ሰሚ ችሎት ነው ይግባኝ ያሉት ሰበር ሰሚ ችሎት ወደ ታችኛው ፍርድ ቤት ይመለስ ብሎ መለሰውና ታችኛው ፍርድ ቤት ነው ' ነጻ ናቸው ' ያላቸው።
ሞባይሏ በደህንነት ምርመራ ነው የተገኘው።
ስልክ ቁጥሯ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ ኮዱ በእሷ ቁጥር ወጥቶ ከእሷ በኋላ የማን የማን ሲም ካርድ እንደገባ የሚያሳይ ዝርዝር ነው ከአዲስ አበባ የተላከው። በዝርዝሩ ስልክ ቁጥር፣ ፎቶ ጭምር ነው የወጣው።
በማስረጃው እስከ 13/12/2015 ዓ/ም እሷ ይዛው እንደነበር በቀን 16 ዕለት ደግሞ አንገሶም ገብረስላሴ ይዞት እንደነበር፣ እስከ መስከረም 8 በእነሱ አንገሶም እና ያሬድ ጋር እንደነበር ፤ ከነሱ ወጥቶ ደግሞ ወደ ሌላ ሰው ሄዷል። የነሱ ዝርዝር አለ።
መጨረሻ ላይ ደጅን የሚባል ሰው በGPS ተፈልጎ መቐለ ውስጥ ቀፎው ከእሱ እንደተያዘ ነው ዝርዝሩ የሚገልጸው።
ይህ ዝርዝር መረጃ ከፌዴራል መረጃና ደህንነት የተገኘ ነው።
አሁን የተፈጠረው ' ኦሪጅናሉ የለም የዶክመንቱ ከአዲስ አበባ ይምጣ ' ተባለ። ሰዎቹ ከአዲስ አበባ መጥተው ማስረዳት አለባቸውም ተባለ። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ወደ መቐለ መምጣት አይችሉም ሲባል ፍርድ ቤቱ ' እሺ ከመቐለ ፖሊስ መጥቶ ማስረዳት የሚችል ካለ መጥቶ ያስረዳ ' አለ ከዛ ኮማንደር መጡና አስረዱ። ጥያቄ ነበረው ብዙ። ዳኞቹ ግራ ገብቷቸው ነበር ጥያቄ ያበዙ ነበር።
ዳኛው እራሱ የአሁኑ ሞባይል ካቀረባችሁት ማስረጃ ጋር ኮዱ አይገናኝም አለ። ከዛ ኮማንደር ' ከኔ በኋላ ተቀይሮ ሊሆን ይችላል ' አሉ።
እኔም ጥርጣሬዬ እንደዛው ነው። ከአዲስ አበባ በደምብ ተጣርቶ መጥቶ አሁን ፍርድ ተፈርዶ ከአመት በኋላ ኮድ የሚቀየርበት ምክንያት ምንም ሊኖር አይችልም። ወይ ቀፎው ተቀይሯል ወይ የሆነ ነገር ተሰርቷል።
ዳኞቹ ' አንድ አይነት አይደለም ' ሲሉም ነበር ማስረጃው። ዳኞቹ ቀፎውን ከፍተው አይተውታል። እንዴት እንደበራ አላውቅም እስከ አመት ቁጭ ያለ ሞባይል አብርተው አዩ።
ኮማንደሩ ' ምናልባት ቀፎው ተቀይሮ ሊሆን ይችላል ' አለ።
በተጨማሪ ስለሞባይሉ የሚያሳየው ፋይል ' ጠፍቷል ' ሲባልም ነበር። ፋይሉ እንዴት ጠፋ ? ስንል ' ይግባኝ ተብሎ ከክልል ፍርድ ቤት ሲወጣ ከክልል ፍርድ ቤት ነው የጠፋው ' ነው ያሉት። እንዴት እንደጠፋ አናውቅም። እኛ እነሱን አምነን ነው ህግ አምነን ነው የምንቀሳቀሰው ሌላ ኃይል የለንም እኛ።
አሁን ፍርዱ ተቀልብሶ በነጻ እንዲፈቱ ተወስኗል።
ይህ ለቤተሰብ ከባድ ነው። ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው። አዲስ ሀዘን ነው የሆነብን። ለእኛ እዚህ ለምንቀረው እንጂ ለሷ ምንም ነገር አይደለም።
ትንሽ በአእምሮ እረፍት አግኝተን ነበር። አሁን ተመስሎ ነጻ ነው ሲባሉ ቤተሰቡ ሁለተኛ ሀዘን ነው ቁጭ ያለው። እንደ አዲስ ሀዘን ነው ቁጭ ያልነው። ስናለቅስ ነው የዋልነው። "
የዘውዱ ሃፍቱ ግድያ የፍርድ ሂደት ከመነሻው አንስቶ በብዙ ድራማ የታጀበ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ - መቐለ ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል።
የተከሳሽ ወገኖች ችሎት ውስጥ ረብሻና ግርግር መፍጠር፣ መበጥበጥ፣ ዳኞችን " እንደመስሳችኋለን ቀናችሁን ጠብቁ " እያሉ ሲያስፈራሩ ነበር።
ልክ ውሳኔ ሊሰጥ ሲልም በረብሻ ምክንያት ውሳኔዎች ቀናቸው ሲቀየር ነበር።
በተጨማሪ ወንጀለኞቹ ፍርድ እንደማይቀርላቸው ሲያውቁ ፍርድ እንዲቀልላቸው " የቆየ ህመም አለብን " ቢሉም ምንም አይነት የቆየ ህመም እንደሌለባቸው በህክምና ማስረጃ ሁሉ ተረጋግጦ እድሜ ልክ እስራት ነው የተፈረደባቸው።
ከዓመት በኋላ ግን ከአሰቃቂ ግድያ ወንጀሉ " ነጻ ናቸው " ተብሎ ተፈርዶላቸዋል። ቤተሰብም ዳግም ሀዘን ተቀምጧል።
ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia