#ችሎት
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#ችሎት
የፌደራል ፖሊስ በኢህአፓ አባላት አቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እና በፓርቲው ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ ላይ " የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል " ሲል ወንጅሏል።
ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።
ፖሊስ ለፍርድ ቤት እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ ከህወሓት፣ "ጽምዶ" እና ከሌሎች "ጸረ ሰላም ኃይሎች" ጋር በመቀናጀት ፦
- በአዲስ አበባ አባላትን በመመልመልና በማደራጀት፣
- የጸጥታ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመሰለል፣
- ለ "ፅምዶ" ቡድን መረጃ በማቀበል እንዲሁም የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና የሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ክንፎችን በማደራጀት ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ወንጅሏቸዋል።
በተጨማሪም ፖሊስ፣ ተጠርጣሪዎቹ የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር በማሰብ በውጭ ሀገር በሚገኙ መገናኛ ብዙኃን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያሰራጩ ነበር በማለት ወንጅሏቸዋል። በፖሊስ ማመልከቻ በስም የተጠቀሱት መገናኛ ብዙኃን አንከር ሚዲያ፣ ኢትዮ ፎረም እና ኢትዮ 360 ናቸው።
ግለሰቦቹ "ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ‘በኃይልም ቢሆን ማስወገድ አለብን’፣ ‘በየትኛውም አካባቢ የሚደረግ የትጥቅ ትግል አግባብ ነው’ በማለት"፣ "ለህዝቡ የትጥቅ ትግል የመጨረሻ አማራጭ መሆን እንዳለበት" መናገራቸውን ፖሊስ በማመልከቻው ላይ ጠቅሷል።
ሶስቱ ተጠርጣሪዎች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ላይ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተቋማት እና በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ላይ "የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ " እንደሆነ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገልጿል።
የተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ጉዳይ " ውስብስብ " እና " ሰፊ ጊዜ " የሚፈልግ በመሆኑ የምርመራ ስራ ለማካሄድ 14 ቀን ጠይቋል።
ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ሁሉንም ውንጀላ በመካድ፣ “በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እናምናለን፤ መንግስትን በኃይል የመገልበጥ ዓላማ የለንም " ብለዋል።
አቶ አበበ፥ " መንግስት እንዲስተካከል የሚጥሩ " መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። " ሀገር አለኝ፣ ልጆች አሉኝ። በሰላማዊ ትግል ነው የምናምነው " ብለዋል።
ችሎቱ፣ ፖሊስ ግለሰቦቹን በሽብርተኝነት የጠረጠረበትን በመገናኛ ብዙሃን የተላለፉ መልዕክቶች የሽብር ክስ እንደሚያቋቁም ለመረዳት እና በዋስትናው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንደሚያስፈልገው ገልጿል።
በዚህም መሰረት ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በመገናኛ ብዙሃን አድርገውታል የተባለውን ንግግር በማስረጃነት ይዞ ለነገ ሐሙስ ሐምሌ 30፤ 2018 እንዲቀርብ አዝዟል።
ማስረጃዎቹን መርምሮ በዋስትና ጥያቄው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለአርብ ነሐሴ 1 ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።
ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia