ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም።
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም።

የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት መለቀቁን በመግለጽ ተማሪዎችና ወላጀችን የሚያደናግር ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

እስካሁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ የፈተናው ውጤት ይፋ ስለመደረጉ በይፋ አላሳወቀም።

ትክክለኛ የተረጋገጡ መረጃዎች ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ የሚገኙ በመሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች ሀሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ የተለያዩ አካላትና ገጾች ትጠነቀቁ ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ያስተላልፋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የፈተናው ውጤት ሰኞ ወይም እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል።

ውጤት ሰኞ ዕለት ይፋ ያልተደረገ ሲሆን እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የፈተናው ውጤት ይፋ ሲደረግ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ በይፋ የሚያሳውቅ ሲሆን እንዴት ማየት እንደሚቻልም ተቋሙ ገለጻ ያወጣል። እኛም ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች