ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#AddisAbaba

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#AddisAbaba
#AddisAbaba
#ደመራ

ከነገ ረፋድ 5:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

ነገ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

ከረፋድ ከ5:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ፦

- ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች
- ከቦሌ ኤርፖርት  ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ  ላይ እና ታች
- ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
- ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል  አደባባይ ለገሃር መብራት
- ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ
- ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር  ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ
- ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ
- ከካዛንቺስ መብራት ወደ  መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ  ዝግ   ይሆናሉ።

ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት  በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ  መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች