ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#Ethiopia #Dangote #Djibouti

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#Ethiopia #Dangote #Djibouti
#Ethiopia #Dangote #Djibouti

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በጅቡቲ ተገኝተው፣ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና ከዳንጎቴ ግሩፕ መስራች አሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን ጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ አዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክትን ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች የሚገነቡ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናሎችን ያካተተ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ትብብር እንደሚተገበር አመልክተዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ፕሮጀክቱ የነዳጅ ማጓጓዣ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ የኢትዮጵያን የኃይል ዋስትና ለማጠናከር እንዲሁም በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለውን የንግድ መስመር የበለጠ ፈጣንና ዘላቂ ለማድረግ ያግዛል።

ፕሮጀክቱ ከነዳጅ ማጓጓዣ መሠረተ ልማት ባለፈ፣ የአፍሪካውያንን ኢንቨስትመንትና የጋራ ልማት ለማሳደግ የታለመ ሰፊ ኢንቨስትመንት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች