ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

⚠️ GRAPHIC CONTENT

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
⚠️ GRAPHIC CONTENT
ይህ ቪድዮ አስደንጋጭና የሚረብሽ ይዘት ስላለው በጥንቃቄ ይመልከቱ።


በአሜሪካ በመብረቅ ተመቶ በተአምር ከሞት የተረፈው ግለሰብ መነጋገሪያ ሆኗል።

በአሜሪካን፣ ኒውዮርክ ውስጥ " ስታተን አይላንድ " የተባለ አካባቢ ነዋሪ የሆነው ቶማስ ፋህሚ የተባለ ግለሰብ ከመኪናው 15 እስከ 20 ጫማ ርቀት ላይ ሳለ በድንገት በመብረቅ ተመቶ በተአምር ከሞት ተርፏል።

ግለሰቡ ከመኪናው ወርዶ ብዙም ሳይሄድ ነው በከባድ መብረቅ ተመትቶ ከሞት አፋፍ የተረፈው።

በአካባቢው በነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ የተከሰተው ይህ አስደንጋጭ አደጋ ፋህሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የስነ-ልቦና ስቃይ ፈጥሯል።

በመብረቅ በተመታበት ወቅት በሁለቱም እግሮቹ ላይ ከባድ የመቃጠል ስሜት፣ የመደንዘዝ እና ከፍተኛ የህመም ስሜት እንደተሰማው ምስክርነቱን ሰጥቷል።

አደጋው ከተከሰተ በኋላ " በሌላ መብረቅ እመታለሁ " የሚል ከፍተኛ ስጋትና ፍርሃት አድሮበት እንደነበር ተናግሯል።

በአሁኑ ወቅት በህክምና ክትትል ከጉዳቱ በማገገም ላይ ያለው ቶማስ ፋህሚ፣ ይህ አስከፊ አደጋ በህይወት ላይ ያለውን አመለካከት ሙሉ በሙሉ እንደቀየረው ይናገራል።

አደጋው ህይወትን ማድነቅ፣ ንጹህ አየርን መተንፈስ፣ ለዕለት ተዕለት ኑሮ ትልቅ ዋጋን መስጠት እንዳለበት አስተምሮታል። እንዲሁም ህይወትን በጭንቀት ውስጥ ማሳለፍ እንደማይገባ ግንዛቤ እንደጨበጠበት ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከ 'ስካይ ኒውስ' ነው ያገኘው።

ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች