#Update
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#Update
በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እንዲከታተሉ አቃቢ ህግ አቤቱታ አቀረበ።
• በአቤቱታው ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ 9 ሰዓት ቀጠሮ ተሰጥቷል።
በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በ 400 እና 500 ሺ ብር የገንዘብ ዋስትና ጉዳያቸውን ከውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል።
በክስ መዝገቡ በ 5ኛ ተከሳሽነት የተቀመጠው መንሱር ጀማልም የዋስትና መብቱ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተወስኖለት ጉዳዩን ከውጭ ሆኖ እተተከታተለ ይገኛል።
ተከሳሾቹ አቅርበውት የነበረው የክስ መቃወሚያ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሐምሌ 29/2018 ዓም በዋለው ችሎት ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጓል።
ችሎቱ የክስ መቃወሚያው ላይ ብይን ለመስጠት በቀጠሮ ላይ በነበረበት ሂደት ቀደም ብሎ 1ኛ(ሰራዊት)፣ 2ኛ(ሰለሞን)፣ 3ኛ(ይገረም)፣ 4ኛ(ዳንኤል)፣ 6ኛ(ካሊድ)እና 7ኛ(አብርሃም) ተከሳሾች እንዲሁም ለ2ኛ እስከ 4ኛ፣ 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆነው ጠበቃ አበባው አበበ የክስ ሂደቱ ሳይጠናቀቅ ባለቤትነቱ የአቶ ተክለሀይማኖት አዳነ የሆነ እግረኛው በተሰኘ ሚዲያ ላይ በመቅረብ የተሰራውን ዘገባ በተመለከተ ህግን መተላለፍ እና ችሎቱን ተጽዕኖ ውስጥ መክተት ነው በሚል አቃቢ ህግ አቤቱታ አቅርቧል።
አቃቢ ህግ ያቀረበው ዝርዝር አቤቱታ በከፍተኛ የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾች እና ጠበቃቸው፣ የተከሰሱበት የክስ መዝገቡ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ በችሎት ውሳኔ ያልተሰጠበት ሆኖ ሳለ እንዲሁም ከቀረባበቸው ክስ አውድ እና ማስረጃ ዝርዝር ውጪ የሆነ ነገር በሚዲያ ላይ ቀርበው በመናገር የፍትሕ ሂደቱን ተጽዕኖ ውስጥ ለመክተት እና ምስክሮችን ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ሞክረዋል የሚል ነው።
ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ባለ አራት ገጽ የጽሁፍ አቤቱታ እንደገለጸው በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል የተከሰሱት "እነ ሠራዊት ፍቅሬ" (6 ተከሳሾች) እና ጠበቃቸው አቶ አበባው አበበ "እግረኛው ሚዲያ" በተባለ የዲጂታል ሚዲያ አማካኝነት የፍርድ ቤቱን ነጻነት የሚጋፋ ተግባር ፈጽመዋል ብሏል።
ተከሳሾች እና ጠበቃቸው ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ሁኔታ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተመለከቱት የቪዲዮ ስርጭት "ህዝቡ ስለጉዳዩ የተዛባ ሀሳብ እንዲይዝ ማድረጋቸውን እና በግለሰቦች አቤቱታ ላይ ተመስርቶ ሃሰተኛ ክስ እንደቀረበባቸው ለማስመሰል መሞከራቸውን ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።
ይህም ፍርድ ቤቱ ላይ ጫና ለመፍጠር እና ሕዝብ ዘንድ መንግሥት መ/ቤቶች ላይ ያለውን አመኔታ እንዲያጣ ለማድረግ ሞክረዋል ብሏል።
ዐቃቤ ሕግ በማብራሪያው፣ ተከሳሾች ተከሰው ለችሎቱ የቀረቡበት የክስ አይነት በአለም ላይ የፖንዚ ማታለል(ሲታይ የሚያማልል ነገር ግን የማይፈጸም የንግድ ሃሳብ ማመንጨት) በመባል ከሚታወቅ የማታለል አይነት ሃሳብ ያለው ነው ብሏል።
በአለም ላይ በሚታወቀው በእዚህ ማታለል አይነትም በርካታ ዜጎች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደተበዘበዙ ጠቅሷል።
ሆኖም አርቲስቶቹ እና ቲክቶከሩ የቀረበባቸው ዋነኛ የክስ ጭብጥ ድርጅቱ የተመሰረተዉ፣ አማላይ ንግድ ሃሳብ የቀረበዉ፣ ይህዉ ዉል ለተወሰኑ ሰዎች የተፈጸመዉ እና ለቀሪ ሰዎች ያልተፈፀመዉ በታቀደበት የማታለል ሃደት ነዉ ወይስ አይደለም?
የአሁን ተከሳሾች በማታለል ሂደቱ ተሳትፎ አላቸዉ ወይስ የላቸዉም የሚል ሆኖ ባለበት ተከሳሾች ማታለሉ ሀሰት ነዉ በሚል ሙሉዉን እዉነታ በማያስረዳ ቀደም ብሎ ለማታለል በተዘጋጀ ማስረጃ አስደግፈዉ በሚዲያ ለማስረዳት የሚያደርጉት ጥረት ዋነኛዉን የክርክር ሃደት የሚጎዳ እና ፍርድ ቤት ላይ ጫና የሚፈጥር ነዉ ብሏል፡፡
ይህ የተከሳሾች ተግባር በወንጀል ሕግ አንቀጽ 457 ስር የተደነገገውን "የፍትሕ ሂደትን በማዛባት" ወንጀል የሚያቋቁም መሆኑን ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
እነዚህን እና መሰል አቤቱታዎችን ለችሎት ያቀረበው አቃቢ ሕግ
- ተከሳሾች፣ የሚዲያው ባለቤት እና ጠበቃቸው በፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን ለምን እንደፈጸሙ እንዲያስረዱ እንዲሁም በወንጀን ህግ አንቀጽ 457 ስር በቀጥታ እንዲቀጡ እንዲወሰን፤
- ተከሳሾች የተሰጣቸውን የዋስትና ግዴታ እያከበሩ ስላልሆነ የዋስትና መብታቸው ወርዶ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከራከሩ እንዲወሰን፤
- ፍ/ቤቱ ድርጊቱን በቀጥታ መቅጣት የማይችል ከሆነ አቃቢ ህግ የወንጀል ምርመራ የማድረግ እና ክስ የማቅረብ ስልጣኑን ተጠቅሞ ምርመራ የሚጀምር እና ተከሳሾችን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጎ ክስ የሚያቀርብ መሆኑን በመረዳት በሚዲያ የተላለፈው ዘገባ እንዲነሳና ይቅርታ እንዲጠየቅበት ትዕዛዝ እንዲሰጥ የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርቧል።
በቀረበው አቤቱታ መሰረት ተከሳሾች በዛሬው ዕለት በችሎቱ በመቅረብ ምላሽ ያሉትን አሰምተዋል።
በምላሻቸውም "ታስረን በነበርንበት ጊዜ ስማችን ጠፍቷል የተለያዩ ጸያፍ ቃላት ተነግሮብናል፣ ፍርድ ቤቱ ሳይወስንብን ማህበራዊ ሚዲያው ወስኖብናል"።
"እኛ ስራችን ህልውናችን የተመሰረተው በስማችን እና በዝናችን ላይ ስለሆነ እሱ ስማችንም ስለጠፋ ለማደስ እና ለማስተካከል ነው ወደ ማህበራዊ ሚዲያው የሄድነው በቆይታችንም የህግ ጉዳዮችን ላለመንካት ሞክረናል" ብለዋል።
በተጨማሪ በቀረበባቸው ክስ ምክንያት ከተለያዩ ድርጅት ጋር ገበተዋቸው የነበሯቸው ውሎች የተቋረጡ ስለመኖራቸውም አንስተዋል።
እንዲሁም "እየሰራን ያለነው ከተበዳዮች ጎን ሆነን ነው በቃለ መጠይቁም ወቅት የጣስነው የብሮድካስት አዋጅም ሆነ ህግ የለም" የሚሉ ጭብጦችን በማንሳት ተከራክረዋል።
የእግረኛው ሚዲያ ባለቤት ተክለሃይማኖት አዳነ በችሎቱ በመገኘት በሰጠው ምላሽ ቃለ መጠይቁን ያደረገው ከአርቲስቶቹ በመጣ ጥያቄ መሆኑን አብራርቷል።
በተጨማሪም ከእዚህ ቀደምም ከክሳቸው በፊት ከአርቲስቶቹ አንዳንዶቹን አቅርቦ የነበረ መሆኑን በማስታወስ ያንኑ ተመሳሳይ ስራ መስራቱን ከቃለ መጠይቁ በፊትም ጠበቃ ማማከሩን በመግለጽ ቃሉን ሰጥቷል።
በዛሬው ችሎት መንሱር ጀማል እና ወንድም ካሊድ እንዲሁም የተከሳሽ ጠበቃ አበባው አበበ አልቀረቡም።
የግራ ቀኙን አቤቱታ ያደመጠው ችሎቱ በቀረበው አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ 9 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia