#Update
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#Update
" ኦነግ ሸኔ ኮሬንም የሎጂስቲክስ ምንጭ አድርጎ በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተደርጎ በምዕራብ ጉጂ ዞን አመራር የተሰጠው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " - አቶ አሸብር በዙ፣ የኮሬ ዞን ኮሚኒኬሽን ኃላፊ
" መረጃው እየሞተ ያለውን ሕዝብ የሚወነጅል ነው ! "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በኮሬ ዞን፣ ጎርካ ወረዳ፣ ሁለት ወጣቶች በሞተር ሳይክል ከዝጆላ ወደ ኬሌ ከተማ እየተጓዙ ባሉበት 'ቦኮሶ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጥቃት ተፈጽሞባቸው ሕይወታቸው ማለፉን አስመልክቶ ባወጣው ዘገባ የሁለቱንም ዞኖች የጸጥታ መዋቅሮች ማነጋገሩ ይታወቃል።
የኮሬ ዞን ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ፣ የምዕራብ ጉጂ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ኦኔግ ሸኔ " ኮሬንም እንደ የሎጂስቲክስ ምንጭ እየተጠቀመ... " በሚል የሰጡትን መረጃ ተቃውሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አስመልክቶ የኮሬ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ አሸብር ገዙን አነጋግሯቸዋል።
አቶ አሸብር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " የምዕራብ ጉጂ ዞን የጸጥታ መዋቅር ተጠሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ እና በምድር ላይ ያለውን ሀቅ የካደ፣ እየሞተ ያለውን ሕዝብ የሚወነጅል እና አደገኛ አካሄድ ያለው ነው " ብለዋል።
አቶ አሸብር ፥ " በአሸባሪነት ተፈርጆ ሀገር እያተራመሰ፣ ሀገር በማፍረስ ተግባር ላይ የተሰማራውን ሸኔ፣ ልክ እኛ የሎጂስቲክስ ምንጭ ሆነን እንደምንደግፍ አድርጎ የሰጠው መግለጫ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" በጉጂ እና በኮሬ መካከል የረጅም ጊዜ አብሮ የመኖር ትስስር አለ፤ በጋብቻም፣ በደምም የተሳሰረ፣ ገበያም አብሮ ይገበያይ የነበረ ሕዝብ ነው " ያሉ ሲሆን፣ የነበረው ሰላም ይበልጥ እየደፈረሰ የሄደው በሀገራችን በሰሜኑ አካባቢ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ በአካባቢው ሰፍሮ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ወደዚያ መንቀሳቀሱን ተከትሎ መሆኑን ጠቁመዋል። የጸጥታ ችግር እስካሁን አለመብረዱንም አስረድተዋል።
" ፀረ-ሰላም ኃይሉ ራሱ የመሸገውም፣ እየተንቀሳቀሰ ያለውም በኦሮሚያ ክልል ነው፤ በምዕራብ ጉጂ ዞን በራሳቸው ክልል ነው " ያሉ ሲሆን " ሰው በወጣበት ነው እየሞተ ያለው፣ መንገድ ማለፍ አልተቻለም፣ እርሻ እያረሰ በእርሻው ነው እየሞተ ያለው። አንድ ቀን ሰላም ከተዋለ፣ አንድ ቀን ሰላም ከተባለ፣ አንድ ቀን ሰው ሳይሞት፣ ሰው ሳይቆስል፣ ሳይደማ ከዋለ እና ካደረ፣ እሰይ፣ እግዚአብሔር ይመስገን እያልን ነው ያለነው " በማለት የአካባቢው የጸጥታ ችግር ሥር የሰደደ ስለመሆኑ አብራርተዋል።
" አንድ የመንግሥት ኃላፊነት ያለበት ሰው ሕዝብን የመጠበቅና ለሕዝብ ደህንነት መቆርቆር ሲገባው፣ የኮሬ ዞን እነዚህ የፀረ-ሰላም ኃይሎች የሎጂስቲክስ ምንጭ ሆኖ እያገለገለ በማስመሰል የሰጡት መረጃ ሊታረም ይገባል " ሲሉ አስገንዝበዋል።
አቶ አሸብር፣ ችግሩ በሁለት ክልሎች፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ፣ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚከሰት በመሆኑ፣ የታጠቁትን የጸረ-ሰላም ኃይሎች ለማጽዳትና ለሕዝቡ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሁለቱ ክልሎች እና የፌደራል መንግሥት አጣዳፊ ጣልቃ ገብነትና የጋራ መፍትሔ ያስፈልጋል ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ የሚያቀርብ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia