ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሲቲ ምን ያህል ተጨዋች ያስፈርማል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሲቲ ምን ያህል ተጨዋች ያስፈርማል ?
ሲቲ ምን ያህል ተጨዋች ያስፈርማል ?

ማንችስተር ሲቲ በርካታ ተጨዋቾች የሚለቁ በመሆኑ በዝውውር መስኮቱ ብዙ ስራዎች ይጠብቁታል ተብሏል።

እስካሁን ከሶስት ተጨዋቾቹ ጋር የተለያየው ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ ተጨማሪ ተጨዋቾች እንደሚወጡ ተነግሯል።

ክለቡ በሚለቁ ተጨዋቾች ልክ ተጨዋች ለማምጣት ባያቅድም በርካታ ፊርማ እንደሚኖር ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲ አሁን ላይ በርካታ ዝውውሮች ለመፈፀም ሲዘጋጅ :-

- የቀኝ መስመር ተሰላፊ
- የመሐል ሜዳ ተሰላፊ እና
- የክንፍ ተጨዋች ለማስፈረም ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በቀጣይ እነማን ሊለቁ ይችላሉ ?

- ማቲኦ ኮቫቺች
- ጄምስ ትራፎርድ
- ኒኮ ጎንዛሌዝ እና
- በቶተንሀም የሚፈልገው ሳቪንሆ ክለቡን ይለቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ኦማር ማርሙሽ ፤ ሬንደርስ እና ሩበን ዲያስ በክለቡ ያላቸው ቆይታ የተረጋገጠ አይደለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች