ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በአለም ዋንጫው የጨዋታ ማጭበርበር ነበር ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በአለም ዋንጫው የጨዋታ ማጭበርበር ነበር ?
በአለም ዋንጫው የጨዋታ ማጭበርበር ነበር ?

በ ዘንድሮው የአለም ዋንጫ ወቅት የጨዋታ ማጭበርበር ተፈፅሟል የሚል ጥርጣሬ መኖሩ ተሰማ።

በአለም ላይ ያሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ቡድን በተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ ሰባት የጨዋታ ማጭበርበር ምልክቶች ማግኘቱን ገልጿል።

ሙሉ የግኝቱ ሪፖርት ይፋ ባይደረጉም የተወሰኑት ጥርጣሬዎችን አሰራጭተዋል።

በተገኙ ምልክቶች መካከል :-

- የደቡብ አፍሪካ ተጨዋች ዝዋኒ በመጀመሪያ ጨዋታ የተሰጠው ቢጫ ካርድ።

- አንድ አቋማሪ ተቋም ለስፔን እና ኬፕ ቨርዴ ጨዋታ አቻ ውጤት ከ 4 ሚልዮን ዩሮ በላይ መቀበሉ።

- ቫር ፌራን ቶሬስ ሳውዲ አረቢያ ላይ ያስቆጠረውን ጎል ለመሻር 3 ደቂቃ በላይ መውሰዱ ይገኙበታል።

ይሁን እንጂ ፊፋ በአለም ዋንጫው ወቅት ከውርርድ ጋር የተገናኘ ማጭበርበር ስለመከሰቱ የሚጠቁም ምልክት እንዳላየ አስታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች